ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው ጠዋት እትሞዋ

ዘወትር ማክሰኞ ጠዋት ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ሳምንታዊ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም እንደተለመደው በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ የስፖርት ዘገባዎች ላይ ያተኮሩ እና ያልተሰሙም አዳዲስ መረጃዎችን ይዛላችሁ ትቀርባላች፤ የእኛ እና የእርሶ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ የምታቀርብላችሁ ዘገባዎች ከሀገር ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች የሆነው አበባው ቡታቆ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከረጅም ጊዜ በኋላ በቋሚ ተሰላፊነት ለክለቡ እየተጫወተ ስላለበት ሂደት ስለቡድናቸውና ስለ አቋሙ፤ ከደደቢት አስራት መገርሳን በወቅታዊ የቡድናቸው አቋም ዙሪያ ከአዳማ ከተማ በአሁን ሰዓት በሁለገብ የጨዋታ ሚናው ላይ ክለቡን እያገለገለ ያለው ሙጂብ ቃሲም ስለ ክለባቸው ስኬታማነት እና ስለራሱ የጨዋታ ሚና እንደዚሁም  ከባህር ማዶ ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ በክሪስመስ ቡድናቸው ሊያስመዘግብ ስላቀደው ውጤትና የቡድኑ ተጨዋች ዝላታን ኢብራሂሞቪች ራሱን ገና እንደወጣት ልጅ እየቆጠረ ስላለበት ሁኔታ፣ የቼልሲው አሰልጣኝም አንቶኒዮ ኮንቲ በሊጉ የስኬት ስራቸው እየኮሩ ስላለበት ሁኔታ፤ የአርሴናሉ አሌክሲስ ሳንቼዝ ቡድኑን ለሻምፒዮናነት ለማብቃት ስለተዘጋጀበት እና የሊቨርፑሉ ሳዲዮ ማኔም በክሎፕ አሰልጣኝነት ስር ደጋፊዎቻቸውን ለስኬት ሊያበቁ ስለተዘጋጁበት እና የባርሴሎናው ሉዊስ ሱዋሬዝም የክለቡ የምንጊዜም ምርጥ 9 ቁጥር ለመሆን ስለተዘጋጀበት እና ሌሎችም ጣፋጭ እና ምርጥ የመዝናኛ ዘገባዎችንም ሀትሪክ ነገ ይዛላችሁ ትቀርባለች፤ ሀትሪክ እንዳታመልጦት፡፡>

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook