መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2018 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የክለቦች ውድድር የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚዎች ይፋ ሆነዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ

በ2018 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የክለቦች ውድድር የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚዎች ይፋ ሆነዋል።

አጋራ
አጋራ

በ2018 የቶታል ካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ይፋ ሲሆኑ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደቡብ ሱዳኑ አል ሰላም ዋኡ ጋር ተደልድሏል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዚህ ውድድር የበቃው የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆኑ እንደሆነ ይታወቃል።

የሻምፒዮንስ ሊጉ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከየካቲት 2-4 2010 ዓ·ም ወይም እ.ኤ.አ ከየካቲት 9 – 11 2018 የሚደረጉ ሲሆን የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት ቀጣዩ ጨዋታውን ከማዳጋስካሩ ሲኤንኤፒኤስ እና ከዩጋንዳው ኬሲሲኤ አሸናፊ ጋር በ1ኛ ዙር ማጣሪያ ከየካቲት 30 – መጋቢት 2 2010 ዓ·ም ወይም እ.ኤ.አ ከመጋቢት 9 – 11 2018 ድረስ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ካፍ ድረ ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የ3 ጊዜ የደቡብ ሱዳን የክለቦች ዋንጫን ማሸነፍ የቻለው አል ሰላም ዋኡ ይህ ውድድር በታሪኩ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሻምዮንስ ሊግ ጨዋታው ነው። ይህ ዋኡ በተባለው የደቡብ ሱዳን ግዛት ውስጥ የሚገኘው ክለብ 1200 ሰው የሚያስተናግድ ዋኡ የተባለ ስታዲየም ያለው ክለብ ነው፡፡
የቅድመ ማጣሪያው ሙሉ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ተጠባቂዉ የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጲያ ቡና 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በአቤኔዘር አበበ ተጠባቂው 53ኛው የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና 2–1 አሸናፊነት ተጠናቋል።...

ቅዱስ ጊዮርጊስነጌሌ አርሲዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ እና ሰጎኖቹ ነጥብ ተጋርተዋል

በአቤኔዘር አበበ በመጀመሪያ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርሲ ነገሌ ጋር...

ቅዱስ ጊዮርጊስቅድመ ውድድር ዝግጅትዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ቅዱስ ጊዮርጊስ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ...