በ2018 የቶታል ካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ይፋ ሲሆኑ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደቡብ ሱዳኑ አል ሰላም ዋኡ ጋር ተደልድሏል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዚህ ውድድር የበቃው የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆኑ እንደሆነ ይታወቃል።
የሻምፒዮንስ ሊጉ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከየካቲት 2-4 2010 ዓ·ም ወይም እ.ኤ.አ ከየካቲት 9 – 11 2018 የሚደረጉ ሲሆን የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት ቀጣዩ ጨዋታውን ከማዳጋስካሩ ሲኤንኤፒኤስ እና ከዩጋንዳው ኬሲሲኤ አሸናፊ ጋር በ1ኛ ዙር ማጣሪያ ከየካቲት 30 – መጋቢት 2 2010 ዓ·ም ወይም እ.ኤ.አ ከመጋቢት 9 – 11 2018 ድረስ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ካፍ ድረ ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የ3 ጊዜ የደቡብ ሱዳን የክለቦች ዋንጫን ማሸነፍ የቻለው አል ሰላም ዋኡ ይህ ውድድር በታሪኩ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሻምዮንስ ሊግ ጨዋታው ነው። ይህ ዋኡ በተባለው የደቡብ ሱዳን ግዛት ውስጥ የሚገኘው ክለብ 1200 ሰው የሚያስተናግድ ዋኡ የተባለ ስታዲየም ያለው ክለብ ነው፡፡
የቅድመ ማጣሪያው ሙሉ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

አስተያየት ይስጡ