አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የከፍተኛ ሊጉን ተሳታፊ ክለብ ደሴ ከተማን በዋና አሰልጣኝነት መረከቡ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በአሰልጣኝ ዳዊት ታደለ መሪነት ወደ ሀገሪቱ የሊግ ዕርከን ለማደግ ጥረት ሲያደርግ የነበረው ደሴ ከተማ ለ2018 የውድድር ዘመን ለአዳማ ከተማ ረዳት አሰልጣኝነት አሳልፎ ከሰጠው ወጣቱ አሰልጣኝ በኋላ ዘላለም ሽፈራውን አዲሱ አሰልጣኝ በማድረግ ቀጥሯል።
አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝግጅት በአዳማ ከተሜ የጀመረው ክለቡ የቀድሞውን የደቡብ ፖሊስ ፣ አዳማ ከተማ ፣ ደደቢት ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ መቻል ሲዳማ ቡና ፣ ሰበታ ከተማ አሰልጣኝ የአንድ አመት ቆይታን በክለቡ የሚያደርጉም ይሆናል።

- ማሰታውቂያ -


