By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፋሲል ከነማ ያደረኩት ዝውውር ከሻምፒዮን ወደ ሻምፒዮን ያደረኩት ነው”አስቻለሁ ታመነ (ፋሲል ከነማ)
Share
Notification Show More
Latest News
በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የጨዋታ ዘገባ
ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሲዳማ ቡና
የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ
ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ
ዜናዎች ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች መቐለ 70 እንደርታ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስThe BiG Interviewፋሲል ከነማ

“ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፋሲል ከነማ ያደረኩት ዝውውር ከሻምፒዮን ወደ ሻምፒዮን ያደረኩት ነው”አስቻለሁ ታመነ (ፋሲል ከነማ)

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 5 years ago
Share
SHARE

“ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፋሲል ከነማ ያደረኩት ዝውውር ከሻምፒዮን ወደ ሻምፒዮን ያደረኩት ነው”

“እግዚአብሔር ለአዲስ ታሪክ አዘጋጅቶኛል ብዬ ነው የማስበው”
አስቻለሁ ታመነ (ፋሲል ከነማ)

ባለፉት ጥቂት አመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ከታዩት ጠንካራ የመሀል ተከካዮች አንዱ የሆነው እንግዳችንን የትኛውም አሰልጣኝ ቢያገኘው አይኑን አያሽበትም ይህን እድል በማግኘት ቅድሚያው የያዘው የዲላ ከነማው አሰልጣኝ ገ/ክርስቶስ ቢራራ ነው አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ደግሞ በአቅሙ ተማመነበትና ነገውን አይቶ በደደቢት የተከላካይ ስፍራ የማይነቃነቅ ምሰሶ አደረገው..በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ደግሞ ወደ 5 የሚጠጉ አሰልጣኞች አሰልጥነውታል… ከ2014 ጀምሮ ይህን ታጋይ ተከላካይ ማግኘት የቻለው የፋሲል ከነማው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ነው፤ ሁለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤትን አዋቂ ለአፄዎቹ ስኬት ተገናኝተዋል፡፡ በዲሲፕሊን ችግር ፈረሰኞቹ ካገዱትና 20 ሺ ብር ከቀጡት በኋላ ሰኔ 30/2013 ልክ የዛሬ 10 ቀን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለው ውል በመጠናቀቁ ይፈልጉት ለነበሩት ክለቦች እድል ቢፈጥርም ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ በ2014 እና 2015 ከመሀል ሜዳው የማይጠፋው ማስፈራሪያ ለማድረግ አስፈርሞታል… ይሄ የመሀል ተከላካይ አስቻለሁ ታመነ ከሀትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ በርካታ ጉዳዮች አንስቷል ያለፉት ወራቶችን እንዴት እንዳሳለፈ፣ ለጊዮርጊስ ስላስገባው የይቅርታ ደብዳቤ፣ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስለሚናፍቀው ነገር፣ ዝውውሩን እንዴት እንደሚገልፀው፣ ሊያሳካው ስላሰበው ድል፣ እግር ኳስ ለርሱ ምን ማለት እንደሆነ፣ ለዋሊያዎቹ የመሰለፍ ስጋት እንደሌለበት፣ በ2014 ከአስቻለሁ ታመነ ምን መጠበቅ እንዳለብን፣ ለፋሲል ከነማ ግብ ብታስቆጥር ማሊያ ትስማማለህ ወይ? እንዲሁ ለፋሲል ከነማ በመፈረም ህልሜን አሳካው ትል ይሆን ለሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ የሚከተለውን ይመስላል፡፡

ሀትሪክ፡- ያለፉትን ወራቶች እንዴት አሳለፍካቸው?

- ማሰታውቂያ -

አስቻለሁ፡- ያለፉት 2 እና 3 ወራቶች ከባድ ጊዜ እንዳሳለፍኩ ይሰማኛል ለኔ ጥሩ ጊዜ አልነበሩም ማለት ይቻላል።

ሀትሪክ፡- ከእገዳው በኋላ ውድድርም አልቆ እረፍት ነበረና አረፍኩስ ማለት ትችላለህ..?

አስቻለሁ፡- ቅጣቱን ጨምሮ ሲታይ አረፍኩ የሚባለው ጊዜ ረዘም ያለ ነው ብዙ ጊዜያቶችን በግሌ ልምምድ ስሰራ ስለነበር ያን ያህል እረፍት ነው ማለት አልችልም ለኳስ ተጨዋች ደግሞ ከኳስ መራቅ በራሱ ያሰለቻል ያለመድኩት ጊዜ ነበርና ተሰላችቻለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደብዳቤ አስገብተህ ነበርና ምላሹ ምን ነበር…?

አስቻለሁ፡- እኔ የተለየ ነገር አላደረኩም ደብዳቤ ያስገባሁት ላጠፋሁት ጥፋት ይቅርታ የሚጠይቅ ደብዳቤ ነው መመለስ አለመመለስ የቦርዱ ነው የሚሆነው ልመለስ ብዬ ብቻ ሣይሆን የጥፋተኝነት ስሜት ስለተሰማኝ ይቅርታ ብዬ ጠይቄያለሁ.. ያለው እውነት ይሄ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ዋንጫ ሳትወስድ ጥሩ ባልሆነ ታሪክ መሰናበትህ አልከፋህም…?

አስቻለሁ፡- በእንደዚህ አይነት ስሜት መለያየቴ ብዙም ደስ የሚል ነገር የለውም ደስተኛም አላደረገኝም እንኳን ረጅም ጊዜ የቆየሁበት ክለብ አይደለም አንድ አመት ተከራይተህ የቆየህበትን ቤት ስትለቅ ይከብዳል ብዙ ድሎች ያሳካሁበት፣ ስኬታማ የሆንኩበት፣ ጥሩም መጥፎም ጊዜ ያሳለፍኩበት ክለብ በመሆኑ በዚህ አይነት ስሜት ባልለያይ ደስ ይለኝ ነበር፤ ዋንጫ ያገኘሁበት፣ በክለቡ ማሊያ ታሪክ ከሰሩት ተጨዋቾች አንዱ የሆንኩት፣ ሻምፒዮንስ ሊግ 16ቱ ውስጥ ሲገባ የነበርኩበት፣ 4 አመት ተከታታይ ዋንጫ የወሰደ ቡድን ውስጥ አባል ሆኜ ብዙ ድሎችን አሳክቻለሁ፤ እግዚአብሔር የፈቀደው ነው የሚሆነው..

ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስን በመልቀቅህ የሚናፍቅህ ትቼው በመሄዴ ይቆጨኛል አጣሁት የምትለው ነገር ምንድነው…?

አስቻለሁ፡- አሁን ወደ አዲስ ክለብ ነው የሄድኩት እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነው ሁሉ ነገር የሚሆነው እግዚአብሔር ለአዲስ ታሪክ አዘጋጅቶኛል ብዬ ነው የማስበው… በርግጥ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመልቀቄ ካሳለፍኩት ረጅም ጊዜ አንፃር ከደጋፊው፣ ከአመራሮቹና በክለቡ ጋር ያለኝ ግንኙነት የሚረሱ አይደሉም በአዲሱ ክለቤ ፋሲል ከነማም የሚያስመሰግነኝ በምስራው ስራ ልክ ነው መመስገኑም መተቸቱም አለ ብዬ ነው የማስበው…

ሀትሪክ፡- ደጋፊውን በይፋ ተሰናብተህ የምትሄድበት እድል አለማግኘትህ አልቆጨህም…?

አስቻለሁ፡- በቅርብ ወራት ውስጥ የገጠመኝ ፈተና በእግር ኳስ ህይወቴ የገጠመኝ ነው በግል ለነበረኝ ቆይታ በተለያዩ መንገዶች በፌስቡኬ ላይም ደጋፊዎቹን አመሰግኛለሁ አሁንም በሀትሪክ ላይ ደጋፊውን አመራሩን አብረውኝ የነበሩትን ሁሉ አመሰግናለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፋሲል ከነማ ያደረከው ዝውውርን እንዴት ትገልፀዋለህ…?

አስቻለሁ፡- /ሳቅ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትልቅ ቡድን ነው ትልቅነቱም የማይካድ ነው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ መሆኑም ይታወቃል ፋሲልም ባለፉት 4 አመታት ጠንካራ ተፋላሚና ለዋንጫ የሚጫወት ቡድን መሆኑን አስመስክሯል በኔ እምነት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፋሲል ከነማ ያደረኩት ዝውውር ከሻምፒዮን ወደ ሻምፒዮን ያደረኩት ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማን እንዴት መረጥክ…?

አስቻለሁ፡- ከበርካታ ክለቦች የእናስፈርምህ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ ምርጫዬን ፋሲል ከነማ አድርጌያለሁ የዘንድሮ ሻምፒዮን ነው በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግም ላይ ተሳታፊ በመሆኑና የተሻለ ጉዞ ማድረግ የሚችል ቡድን ስለሆነ ወደ ፋሲል ተጉዣለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ባለፉት 3 አመታት ያጣኸውን የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ በፋሲል ከነማ ማሳካትህን አመንክበት…?

አስቻለሁ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነቴ በሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ እፈልጋለሁ ስብስቡም ስታየው ሻምፒዮን ቡድን ነው ውጤታማ ለመሆን የግድ ወደ ፋሲል መጓዝን መርጫለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- የፋሲል ከነማ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅምስ አላማለለህም…?
አስቻለሁ፡- /ሳቅ በሳቅ/ ለጥቅማ ጥቅምማ ሌሎች ክለቦች የተሻለ አቅርበውልኛል አንዳንዴ ገንዘብን ብቻ ብሎ ወደማይሆን ክለብ አትሄድም የሚመጥነኝ መሆኑ ትላልቅ ተጨዋቾችን መያዙ በብሔራዊ ቡድን የማውቃቸው ጓደኞቼም መኖራቸውን ከግምት አስገብቼ እንጂ ጥቅማ ጥቅምን ብቻ አላስቀድምም፡፡

ሀትሪክ፡- ዝውውር ላይ ካናገሩህ ክለቦች መሀል ለአንዱ 2߀߀ ሺ ብር የወር ደመወዝ ጠየቅክ አሉኝ.. እውነት ነው…?

አስቻለሁ፡- /ሳቅ/ ይሄ ፍፁም ውሸት የሆነ መረጃ ነው ያናገሩኝን የትኞቹንም ክለቦች በዚህ ደረጃ የጠየኩት የለም የሚገባኝን ጠይቄ ከፋሲል ከነማ ጋር መስማማቴን ብቻ ነው የማውቀው፡፡

ሀትሪክ፡- ለፋሲል ከነማ ስትፈርም የትኛውን ተጨዋች አብሬው በመጫወቴ ደስተኛ አድርጎኛል ትላለህ….?

አስቻለሁ፡- ሁሉንም ስላገኘሁ ተደስቻለሁ እገሌ ከእገሌ ብዬ አልለይም ቡድን በአንድ ሰው ስለማይገነባ አንድ ተጨዋች ላይ አላተኩርም፡፡

ሀትሪክ፡- አዎ ቡድን በአንድ ተጨዋች አይገነባም.. ግን የተሻለ ቅርበት ያለው ተጨዋች ሊኖር ግን ይችላል…?

አስቻለሁ፡- /ሳቅ/ ያው ከሁሉም ጋር መጫወት እፈልጋለሁ ትላልቅ ተጨዋቾች የሞሉበት ስለሆነ እከሌን ብዬ ለይቼ አልጠራም ከሁሉም ጋር በመጫወቴ ደስተኛ ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡- ስለ ፋሲል ከነማ ከዝውውር በፊት የነበረህ ስሜት ምን ይመስላል…?

አስቻለሁ፡- ይህን 3 አመት በተለይ ለዋንጫ የሚፋለም ትልቅ ቡድን ነው ስብስቡም ለረጅም ጊዜ አብሮ የቆየ በመሆኑ ውጤታማ መሆኑ አይቀርም እዚያ ስብስብ ውስጥ የኛ መጨመር ካለው ነገር ላይ ትንሽ ነገር እንጨምራለን ብዬ አስባለው ቡድኑ የተደራጀ መሆኑ መታወቅ አለበት ከቡድኑም ጋር ተዋህደን ጥሩ ስራ እንሰራለን ብዬ አስባለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- በ2001 የነበረ በ2014 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባይታይ የምትለው ነገር ምንድነው…?

አስቻለሁ፡- ይሄማ ዳኝነቱ መስተካከል አለበት የታዩ ስህተቶች መደገም የለባቸውም ስልጠና የሙያ ማሻሻያ በአግባቡ ተሰጥቷቸው አቅማቸውን ማዳበር አለባቸው ብዬ አስባለሁ ሰው ናቸውና ስህተት ሊኖር ይችላል እንኳን እዚህ አደግን ባሉ ሀገራት ላይ የሚገኙ ዳኞች ይሳሳታሉና ማስተከከያ ቢኖር ደስ ይለኛል፡፡

ሀትሪክ፡- እግር ኳስ ለአንዳንዶቹ ስራቸው ነው ለሌሎቹ ግን የሚወዱት ስራቸው ደስታ የሚፈጥርላቸው መዝናኛቸው ነው… ለአስቻለው ታመነስ…?

አስቻለሁ፡- /ሳቅ/ እግር ኳስ ለኔ ስራዬና እንጀራዬ ነው እየወደድኩት የምሰራው ስራ ነው በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡- 2013 በግልህ አሪፍ አመት ነበር ብለህ መናገር ትችላለህ…?

አስቻለሁ፡- ጥሩ አመት ነበር ማለት አልችልም በእግር ኳስ ህይወቴ 2013 ጥሩ ያልሆነ ጊዜ ያሳለፍኩበት አመት ነበር ከጤናም ጋር ተያይዞ ችግር ነበረና ጫና ውስጥ የነበርኩበት አመት ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ከእገዳው ጋር ተያይዞ ቤተሰብ፣ የተወለድክባት ሰፈር አካባቢ የነበረው ስሜት ምን ይመስል ነበር… ?

አስቻለሁ፡- የደረሳቸው መረጃ ልክ አልነበረም አስቻለሁ ተቀጣ ሲባል ወሬውን የሰሙበት ሁኔታ በማይሆን መንገድ ተጣሞ ነበርና በቅርበት ሄጄ የተፈጠረውን ሳስረዳቸው ተቀብለውኛል የአካባቢው ሰው ጋርም የነበረውን ጥሩ ያልሆነ ስሜት ለመቀየር ችያለው ትክክኛ ያጠፋሁት ነገር ተናግሬ አስተካክያለሁ ከቤተሰቤ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ የምማከረውም ከነርሱ ጋር ነውና ይብዛም ይነስም ጥፋት መስራቴን ነግሬያቸው እነርሱ ጋር በደረሰበት ልክ አለመሆኑን ተማምነናል ተረድተውኛል ብዬ አስባለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ለዋሊያዎቹ ያለመጠራት ስጋት አለብህ…?

አስቻለሁ፡- በፍፁም ምንም ስጋት የለብኝም ያልተጫወትኳቸው ውስን ናቸው… በዚያ ላይ ሁሉም ተጨዋች ከዝግጅት እንደሚሄድ መረሳት የለበትም፡፡

ሀትሪክ፡- በስነልቡናም ሆነ በአቅም የተሻለውን አስቻለሁን በ2014 እንጠብቅ… ?

አስቻለሁ፡- /ሳቅ/ በሚገባ… 2014 የተሻለው ጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘውን አስቻለውን መጠበቅ ነው ያለባችሁ… ከእግዚአብሔር ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፋለሁ ብዬ አምናለሁ ከቡድን አጋሮቼ ጋር በመሆን የ2߀013 ድል ይደገማል ብዬ አስባለው፤ በሌሎች ክለቦች ያልታየ ወይም ያልተደገመ ስኬት ይገጥመኛል ብዬ አምናለው፡፡

ሀትሪክ፡- የተፈጠረውን ችግር ለመርሳት የወሰድከውስ አማራጭ የለም…?

አስቻለሁ፡- ብዙውን ጊዜ ያሳለፍኩት ከቤተሰቤ ጋር ነው ዲላ ነበርኩኝና በግሌ በአካባቢዬ ባለ ሜዳ ላይ ልምምዴን ስሰራ ቆይቻለሁ የተለየ የመዝናናት ጊዜ አልነበረኝም ጊዜውን በስራ ነው ያሳለፍኩት፡፡

ሀትሪክ፡- አንተን በተመለከተ ስለ ትዳር ስለ ፍቅር ምንም አይነት መረጃ የለም…ምነው ደበከውሳ…?

አስቻለሁ፡- /ሳቅ/ በቅርቡ ትሰማለህ… /ሳቅ/

ሀትሪክ፡- የዝውውር ገደቡ ቢነሣም የአከፋፈል ሂደቱ ልክ አይደለም የሚሉ ወገኖች አሉ .. ለቋሚም ለተጠባባቂም እኩል ይከፈላል… ይሄ ተገቢ ነው…?

አስቻለሁ፡- ይሄ የሚመለከተው ከፋይ ክለቡን ነው ስፖርተኛው በሰራው ልክ ማግኘት አለበት… ማንም ሲጠይቅ የሰራውን ልክ ነውና ክለቦቹ ሲከፍሉ ነው ለዚህ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ያለባቸው፡፡

ሀትሪክ፡- በኔ ህይወት ጉዞ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል በሚል የምታመሰግናቸው አሰልጣኞች አሉ…?

አስቻለሁ፡- የመጀመሪያው ዲላ ከነማ ያሰለጠነኝ በቅርቡ ወላይታ ድቻና ደቡብ ፖሊስንም ያሰለጠነው አሰልጣኝ ገ/ክርስቶስ ቢራራና አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የቅድሚያውን ምስጋና ይወስዳሉ.. ያም ቢሆን በጊዮርጊስ እና በብሔራዊ ቡድን ያሰለጠኑኝን በሙሉ አመሰግናለሁ አሰልጣኝ ገ/ክርስቶስና አሰልጣኝ ዮሀንስ እድሉን ሰጥተው ለዚህ አብስቅተውኛል ለማለት ያህል እንጂ በኔ የእግር ኳስ ጉዞ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉትን ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ስለ ፋሲል ከነማ ደጋፊ የምትለው ነገር አለ?

አስቻለሁ፡- ደስታቸውን እየገለፁልኝ እንኳን ደህና መጣህ እያሉኝ ያሉት በርካታ ናቸው አመሰግናለሁ የፋሲል ከነማ ደጋፊ ጋር በ2014 በተለይ ስታዲየም መግባት ከተፈቀደ አብሬያቸው ድሉን ባጣጣም ደስ ይለኛል ከደጋፊው ጋር መጫወት ደስ ይላል ብዙ ደጋፊ ስላለው ወደ ሌላ በርካታ ደጋፊ ወዳለው ክለብ ነው የተጓዝኩትና ከነርሱ ጋር ደስታዬን ባጣጥም ደስ ይለኛል፡፡

ሀትሪክ፡- አንድ ተጨዋች ግብ አግብቶ ማሊያ ሲስም ለክለቡ ያለው ፍቅር ይገልፃል ይባላል… ክለብ ስትቀይሩም “ህልሜን አሳክቻለሁ” ትላላችሁ…አንተስ እዚህ ላይ ህልሜን አሳክቻለሁ ማለት ትችላለህ… ?

አስቻለሁ፡- /ሳቅ በሳቅ/ ከባድ ጥያቄ ነው ይለፈኝ

ሀትሪክ፡- ጨረስኩ…..የመጨረሻ ቃል…. ?

አስቻለሁ፡- ለዚህ ያደረሰኝን እግዚብሔርንና ቤተሰቦቼን አመሰግናለሁ… በኔ ህይወት ላይ አንድም ነገር ይሁን ጣል ያደረጉትን በሙሉ ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ በእስካሁኑ የእግር ኳስ ቆይታዬ በተለይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያ ከጎኔ የነበሩ ደጋፊዎች አመራሮች የቡድኑ አባላትንም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

You Might Also Like

በጨምበላላ ዋዜማ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ቀምሷል

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

መቐለ 70 እንደርታ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article “ለቅ/ጊዮርጊስ መጫወት ያለውን አደራና ሀላፊነት አውቄ ነው ፊርማዬን ያኖርኩት” በረከት ወልዴ /ቅ/ጊዮርጊስ/
Next Article የሀድያ ሆሳዕና የፋይናንስ ሃላፊ ቅዳሜ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንዜናዎች

ለሃዋሳው የእግርኳስ ፍልሚያ 12 አርቢትሮች ተመርጠዋል

ዮሴፍ ከፈለኝ By ዮሴፍ ከፈለኝ 5 years ago
​አሜ መሀመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማውን አኖረ
የዋልያዎቹ አሰላለፍ ይፋ ሆናል
የጨዋታ ዘገባ |ነብሮቹ ከአዞዎቹ ጨዋታቸዉን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል !!
Le président de la CAF testé positif pour le COVID-19
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?