By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “ለቅ/ጊዮርጊስ መጫወት ያለውን አደራና ሀላፊነት አውቄ ነው ፊርማዬን ያኖርኩት” በረከት ወልዴ /ቅ/ጊዮርጊስ/
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

“ለቅ/ጊዮርጊስ መጫወት ያለውን አደራና ሀላፊነት አውቄ ነው ፊርማዬን ያኖርኩት” በረከት ወልዴ /ቅ/ጊዮርጊስ/

መሸሻ ወልዴ
መሸሻ ወልዴ 5 years ago
Share
SHARE

“ለቅ/ጊዮርጊስ መጫወት ያለውን አደራና ሀላፊነት አውቄ ነው ፊርማዬን ያኖርኩት”
በረከት ወልዴ /ቅ/ጊዮርጊስ/

“ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ሳመራ ምክንያት ኖሮኝና የሚጠበቅብኝንም ሀላፊነትና አደራ አውቄ ነው ፊርማዬን በክብር ያኖርኩት፤ ከዚህ ቡድን ጋርም ትልቅ ስኬትን የመጎናፀፍም እልም አለኝ” የሚል አስተያየቱን ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ የሰጠው ተጨዋች በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት በወላይታ ድቻ የነበረውን የውል ጊዜ በማጠናቀቁ ከቀናት በፊት ለቅ/ጊዮርጊስ ለሁለት ዓመታት ለመጫወት ፊርማውን ያኖረው የአማካይ ስፍራው ተጨዋች በረከት ወልዴ ነው።

ለኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆናቸው የብሄራዊ ቡድን በመመረጥ በሀገራችን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ /ሴካፋ/ ዋንጫ ለመመረጥ የቻለው እና በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይም ለወላይታ ድቻ በመጫወት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን በውድድሩ ቆይታው ያሳየውና በአጨዋወት ባህሪውም ከቼልሲው ንጎሎ ካንቴ ጋር አመሳስለውት በእሱ ስም እየጠሩት ያለው በረከት ወልዴ ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ከወላይታ ድቻ ጋር ተለያይቶ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ስላደረገው ዝውውር፣ በአዲሱ ቡድኑ ስለሚጠብቀው ሁናቴ፣ በወላይታ ድቻ ስለነበረው ቆይታ፣ በአገራችን አስተናጋጅነት ስለሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫና ስለሚያስመዘግቡት ውጤት እንደዚሁም ከራሱ ብቃት ጋር በተያያዘ አጠር ያሉ ጥያቄዎችን ለተጨዋቹ አቅርበንለት ምላሹን ሰጥቶናል። ቃለ-ምልልሱም እንደሚከተለው ቀርቧል፤ ተከታተሉት።

በወላይታ ድቻ የነበረውን የውል ዘመን አጠናቆ ለቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ለመጫወት ፊርማውን ስለማኖሩ

- ማሰታውቂያ -

“ለቅ/ጊዮርጊስ መጫወትን ያለምኩት ገና ወደ ወላይታ ድቻ የዋናው ቡድን እንዳደግኩ ነው። ያኔ የእነሱን ቡድን በተቃራኒነት መግጠምም ከያዙት የተጨዋቾች ስብስብና ከክለቡ ትልቅነትም አንፃር የራስህን ብቃት ለማሳየት የምትጥርበት ሁኔታም ስላለ ለዚህ ቡድን መጫወትን የማይፈልግ አንድም ተጨዋች የለምምና ወደ ቡድኑ በመግባት ይሄን እልሜን ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ በመጫወት ላሳካው ስለተዘጋጀውኝ በጣም ደስ ብሎኛል”።

ለቅ/ጊዮርጊስ ለመጫወት ፊርማህን ስታኖር ስለ ክለቡ ምን ምን ነገሮችን አውቀህ ነው የመጣከው?

“ወደዚህ ቡድን ዝም ብዬ ጓዜን ጠቅልዬ እንደማልመጣ አስቀድሜ ነው የወላይታ ዲቻ ተጨዋች በነበርኩበት ሰዓት ላይ የማውቀው። ቅ/ጊዮርጊስ ትልቅና በውጤታማነት የታጀበ ክለብ እንደሆነ ከእዛ ውጪም ለዚሁ ቡድን ስትጫወት ያለው አደራና ሀላፊነትም በጣም ከፍ ያለ እንደሆነም ገና ለዚህ ቡድን ለመጫወት ፍላጎትን ካሳደርኩበት ጊዜ ጀምሮም የተረዳሁት ነገር ስላለ በዚህ መልኩ ነው ወደ ክለቡ በመምጣት ፊርማዬን ማኖር የቻልኩት”።

በቅ/ጊዮርጊስ ቆይታው የተሳካ እና በውጤታማነት የታጀበ የጨዋታ ጊዜያቶችን ያሳልፍ እንደሆነ

“ወደ ቡድኑ ስመጣ ብዙ አደራና ሀላፊነት እንዳለብኝ ስለማውቅና ጠንካራ የሚባል ሰው ደግሞ በፈተና ውስጥ ሆኖም የሚያልፍ እንደሆነም ስለማስብ የዚህ ቡድን የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ ስኬታማና ከውጤታማነት ጋር የተሳሰረ እንደሚሆንም እርግጠኛ ነኝ። ምክንያቱም ይሄ ቡድን አሁን ላይ ዋንጫ ካጣ አራተኛ ዓመቱን ይዟል። እኛ አዲስ ተጨዋቾች ወደዚህ ቡድን እንድንመጣ የተደረገውም ይሄን ቡድኑ የማይታወቅበትን ታሪክ ሽረን ቀድሞ ወደሚታወቅበት ሀያልነቱ እንድንመልሰውም ስለሆነ ለዛ ራሴን በጥሩ መልኩ አዘጋጅቼው በቡድኑ የተሳካ ጊዜን አሳልፋለው”።

ለወላይታ ድቻ የአራት ዓመታትን ቆይታ ካደረግክ በኋላ ነው ወደ አዲሱ ቡድንህ ቅ/ጊዮርጊስ ልታመራ የቻልከው፤ ጊዜያቶቹ ለአንተ ምርጥ ሆነው አልፈዋል?

” በጣም፤ ግልፅ የሆነና የታየ ነገር ነው እኮ። ከዓመት ዓመት በችሎታዬ ላይ ለውጦች እንዳሉኝ ምንም ጥርጥርም የለኝም። በተለይም ደግሞ ዘንድሮ በነበረው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ውድድር ላይ በጣም የተሳካ የውድድር ጊዜያትን ያሳለፍኩበትና በራሴም ላይ ከፍተኛ ለውጥንም የተመለከትኩበት እንደዚሁም ደግሞ ለብሄራዊ ቡድን ከመመረጥ ባሻገር ወደ ታላቁ ክለብ ቅ/ጊዮርጊስም ተፈልጌ የመጪው ዘመን ውድድር ላይ እንድጫወትም ፊርማዬን እንዳኖር የተደረግኩበትም ዓመት ስለነበር ያ ሊሆን
በመቻሉ ደስታዬ እጥፍ ድርብም ነው”።

ለወላይታ ድቻ የውድድር ዓመቱ በምን መልኩ እንዳለፈና ከክለቡ መለያየቱን በማስመልከት ስለሚለው ነገር

“ይሄ የውድድር ዓመት ለእኛ በሁለት መልኩ ያለፈ ነው። የመጀመሪያው በሜዳ ላይ እንቅስቃሴያችን ጥሩ ሆነን ሳለ በውጤት ቀውስ ውስጥ የቆየንበት ጊዜ ሲሆን ሌላው ደግሞ ከግማሽ ሲዝን በኋላ በአዲሱ አሰልጣኛችን አማካኝነት ወደ ውጤታማነቱም በማምራት የተጓዝንበት ሁኔታም ነበርና ያን ልመለከት ችያለሁ።
በወላይታ ድቻ የነበረኝን ቆይታ አጠናቅቄ ወደ አዲሱ ቡድኔ ስላመራሁበት ሁኔታ ደግሞ ማለት የምፈልገው ይህ ቡድን እኔን ከስር ኮትኩቶ በማሳደግ ለእዚህ እውቅናና ክብር ያበቃኝ ነው። የዚሁ ቡድን ተጨዋች ሆኜም ነው ለብሄራዊ ቡድንም ልመረጥ የቻልኩቴና ይሄን ባለውለታዬን ክለብ መቼም ሳልረሳው ላመሰግነው እፈልጋለሁ”።

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመርጦ ለሴካፋ ዋንጫው እያደረጉ ስላሉት ልምምድ

“በጣም ጥሩ የሆነና ደስ የሚል ልምምድን በአሰልጣኛችን ውበቱ አባተ አማካኝነት እየተሰጠን ለውድድሩ በመዘጋጀት ላይ ነን። በአካል ብቃቱም በስነ-ልቦናውም ዝግጁም ነን። አብዛኛው ልምምድም ከኳስ ጋር በተያያዘ መልኩ በምን ጊዜ ኳስ መያዝና መጫወት እንዳለብንና በምን ጊዜ ደግሞ ኳሱን እየለቀቅን ወደፊት ማጥቃት ላይ ያተኮረን እንቅስቃሴ መጠቀም እንዳለብንም እየሰራንበት ስለሆነ በእስካሁን ልምምዳችን በጣም ደስተኛ ነን። በጨዋታ ዘመኔ እንዲህ ያሉ ልምምዶች ሁሌም ቢሆን ደስ የሚሉኝና የምመርጣቸው ናቸው፤ ለአገራችን የእግር ኳስ እድገትም የሚያዋጣው ይህ አጨዋወትም ይመስለኛልና ሁሌም ብንጠቀመው በጣም ነው ደስ የሚለኝ”።

ስለ ብሄራዊ ቡድኑ /u-23/ የተጨዋቾች ስብስብ

“ምርጥና ጥሩ አቅም ያላቸው ወጣት ተጨዋቾች ናቸው በአብዛኛው በስኳዱ ውስጥ ተመርጠው የተሰባሰቡት። ለዋናው የብሄራዊ ቡድንም ግብዐት የሚሆኑ ልጆችም በዚሁ ስብስብ ላይ እንደተካተቱና እነዚህ ተጨዋቾችም ጥሩ አቅም እንዳላቸውም አሰልጣኞቹ ከእኛ በላይ ጠንቅቀውም ያውቃሉና በሁላችንም ተጨዋቾች ብቃት ተስፋ ሰጪ ነገርን እየተመለከቱም ነው”።

ለሴካፋው ውድድር ለብሄራዊ ቡድን ስለመመረጡ

” ከዚህ በፊትም ገልጬዋለው የመመረጡን ዕድል አግኝቼ በክለቤ በኩል ሳይነገረኝ ቀርቶ ይሄን ዕድል ወደ ሽረ ለጨዋታ በተጓዝንበት ወቅት አውቄ በእኔ ፋንታ ሌላ ተጨዋች ተመርጦ ይህን ዕድል አጥቼ ነበር፤ በወቅቱ ብዙም አልተከፋሁም። አሁን ይህን የመመረጥ እድል አግኝቼ ውዲቷን ሀገሬን ላገለግላትና ለስኬታማነትም ላበቃት የተዘጋጀውበት ሰዓት ላይ ስለምገኝ በጣም ደስተኛ ነኝ”።

ለብሄራዊ ቡድን ተመርጦ መጫወት ስለሚኖረው ስሜትና በሴካፋው ውድድር ላይ ሊያመጡ ስላሰቡት ውጤት

“የሀገርን ባንዲራ በወከለ መልኩ መለያውን ለብሶ መጫወት መቻል ስሜቱ በጣም ደስ ይላል። ስትጫወት ብዙ ነገርንም ትማርበታለህ። እውቀትንም ትገበይበታለህ። ይህን ካልኩ ዘንዳ በሴካፋው ውድድር እኛ ኢትዮጵያኖች በውድድሩ ላይ ልናስመዘግብ ያሰብነው ውጤት አዘጋጅ ሀገር እንደመሆናችንም ዋንጫውን እዚሁ ለማስቀረት ነው። ይሄን ድል የሚያሳካ ምርጥ አቅምም አለን”።

በሴካፋ የመጀመሪያ የመክፈቻ ጨዋታን ከቀድሞ ድንበራችንና ከአሁኗ ጎረቤታችን ኤርትራ ጋር ስለማድረጋቸውና ስለሚያስመዘግቡት ውጤት

” ከኤርትራ ጋር የሚኖረን ጨዋታ ለእኛ የተለየ አይደለም። ሁሉም ተሳታፊ ሀገራት ለእኛ አንድ ናቸውና ከማንም ሀገር ጋር እንደምናደርገው ግጥሚያም ነው ጨዋታውን የምንመለከተው። ይሄም ጨዋታ ከዛም ውጪ ከምድባችን አንደኛ ሆነን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍም የጥርጊያ መንገዱን የሚያመቻችልንም ስለሆነ ከረጅም ዓመታት ቆይታ በዋላ ወደ አገራችን በመምጣት ሊጫወቱ ከተዘጋጁት የኤርትራ ወንድምቻችን ተጨዋቾች ጋር ደስ እያለን ጨዋታውን በማድረግ እነሱን አሸንፈናቸው ከሜዳ እንወጣለን”።

በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመን ቆይታው ስለ ቀጣይ ጊዜ ራዕዩ

“ብዙ ጊዜ ራዕይ የሚገደብ ነገር አይደለም፤ ሁሌም የተሻሉ ነገሮች እንዲገጥሙህ ታቅዳለህና አሁን ላይ ከማስባቸው ነገሮች ውስጥ ወደፊት ጥሩ ነገርን ሰርቼ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ደረጃ ወደ ውጪ ወጥቶ መጫወት ዋናው ምኞቴ ነው። ይሄን እንደማሳካውም እርግጠኛም ነኝ”።

ስናጠቃልል

“በእግር ኳስ ተጨዋችነት አሁን ለመጣሁበት መንገድ በቅድሚያ ፈጣሪ ሁሌም ይመስገንልኝና በሀሳብና እኔን በማሰልጠኑ ረገድም የብዙ ሰዎች እጅ አለበትና እነሱንና ቤተሰቦቼን ጭምር ለማመስገን እፈልጋለው። በኳሱም ለታላቅ ደረጃ ከመብቃት ባሻገር በአዲሱ ክለቤ ውስጥም ደማቅ የስኬት ታሪክን ማስመዝገብ እፈልጋለው”።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By መሸሻ ወልዴ
Follow:
Editor at Hatricksport website
Previous Article ፉአድ ፈረጃ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል!!
Next Article “ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፋሲል ከነማ ያደረኩት ዝውውር ከሻምፒዮን ወደ ሻምፒዮን ያደረኩት ነው”አስቻለሁ ታመነ (ፋሲል ከነማ)

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
መከላከያኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስ

የ2010 የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜውን ዛሬ ያገኛል።

Muluken Tesfaye By Muluken Tesfaye 7 years ago
ደደቢት አራት ተጨዋቾችን አስፈረመ
ሦስት ኮሚሽነሮች ለሁለት ዓመት ታገዱ
ድሬዳዋ ከተማ “ተበድያለሁ” ሲል ምሬቱን አሰምቷል።
የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾች ልምምድ አቁመዋል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?