የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ሲዳማ ቡና የሦስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ውል ዛሬ አድሷል።

የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ ሲዳማ ቡና በዛሬው ዕለት የሦስት ተጫዋቾችን ኮንትራት አራዘመ። ክለቡን የኋላ ደጀን በመሆን ላለፉት ሁለት አመታት ያገለገለው የሊጉ የወቅቱ ኮከብ ተጫዋች የቀድሞው የአውስኮድ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማ የመሐል ተከላካይ አምበሉ ያሬድ ባዬ ፣ የቀድሞው የደደቢት ፣ ወልዋሎ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም በሲዳማ ቡና ያለፉት ሦስት አመታት ቆይታን ያደረገው የመሐል ተከላካዩ ደስታ ደሙ እና ከሀዋሳ ወጣት ቡድን በ2011 የውድድር ዘመን በማደግ ለዋናው ቡድን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት የቻለው የመስመር ከጥቂው መስፍን ታፈሠ ለተጨማሪ አመት ውላቸውን በክለቡ ማራዘማቸው ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ