ሶስት ሰዓት ላይ የጀመረው የቡሬ ዳሞት እና የኢታንግ ከተማ ጨዋታ በቡሬ ዳሞት አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በውድድሩ ከታዩ ጠንካራ ጨዋታዎች የሆነው የቡሬ ዳሞት እና የኢታንግ ከተማ ጨዋታ ጨዋታው በሙከራዎች መታጀብ የጀመረው በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ነበር ።ተመጣጣኝ በነበረው ጨዋታ የቡሬ ከነማ አምበል አለሙ አረጋ በርካታ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችልም ጎል ማስቆጠር ግን አልቻሉም።

ኢታንግ ከተማዎችም በረጃጅም ኳሶች ወደ ቡሬ ዳሞት የግብ ክልል ቢደርሱም ጠንካራውን የቡሬ ዳሞትን የተከላካይ መስመር ግን ማለፍ አልቻሉም ።
- ማሰታውቂያ -
የመጀመሪያ አጋማሽን ባዶ ለባዶ አጠናቀው የተመለሱት ሁለቱ ቡድኖች ከእረፍት መልስ በርካታ ሙከራዎችን እንዲሁም ሀይል የተቀላቀለበትን ጨዋታ ለመመልከት ችለናል ።
በተደጋጋሚ የኢታንግ ከተማዎችን የግብ ክልል ሲፈትሹ የነበሩት ቡሬ ዳሞቶች በመጨረሻም ጥረታቸው ፍሬ አፍርተው በጨዋታው ምርጥ እንቅስቃሴ ሲያደርግ በነበረው አምበሉ አለሙ አረጋ አማካኝነት ጎል አስቆጥረዋል።ከጎሏ በኋላ ኢታንግ ከተማዎች በረጃጅም ኳሶች ያገኙትን አጋጣሚ ቢጠቀሙም የቡሬ ዳሞት ግብ ጠባቃ አላስቀምስ ብሏቸዋል ።ጨዋታውም በቡሬ ዳሞት አንድ ለዜሮ አሸናፊነት ተጠናቋል።

አምስት ሰዓት ላይ የጀመረው የቦዲቲ ከተማ እና የኩምሩክ ከተማ ጨዋታ በቦዲቲ ከተማ ፍፁም የበላይነት ተጠናቋል።
በብዙ ተመልካች ታጅቦ የጀመረው የሁለቱ ጨዋታ ለተመልካች ሳቢ ነበር ።ቦዲቲ ከተማዎች በተደጋጋሚ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ጎል ቢደርሱም ጎል አካባቢ ላይ ግን የመጨርስ ችግር ይታይባቸው ነበር ።በቀኝ መስመር ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ በነበረው ከፖ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት የቀድሞው የመተሐራ ስኳር ወላይታ ዲቻ ደሴ ከነማ እና ሀላባ ከነማ ተጫዋች የነበረው ተመስገን ሀሜ ፍፁም ቅጣት ምቱን አስቆጥረዋል ።

በጎሏ ይበልጥ የተነቃቁት ቦዲቲ ከተማዎች በተደጋጋሚ የኩምሩክን የግብ ክልል መፈተሻቸውን ቀጠሉ : ከመሐል አማካዩ እዮብ የተሰጠውን ግሩም ኳስ ባለ ልምዱ አጥቂ ተመስገን ልምዱን ተጠቅሞ ግሩም ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በቦዲቲ ሁለት ለባዶ መሪነት ለእረፍት ወተዋል።
ከእረፍት መልስ ተጫዋቾችን ቀይረው የገቡት ቦዲቲ ከተማዎች በተደጋጋሚ ጫና ፈጥረው በርካታ ለግብ የሆኑ ኳሶችን ሲመክኑ በአንፃሩ ኢታንግ ከተማዎች በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማስቆጠር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም ።ከእረፍት መልስ ተቀይሮ የገባው ማሞ አየለ በርካታ ኳሶችን ሲያመክን ውሏል ለጎል የቀረቡ ኳሶችንም ለጓደኞቹ ማቀብ እየቻለ ራሱ ሲሞክር በበረኛው መክኖበታል ።ከብዙ ጥረት በኋላም ማሞ አየለ ሶስተኛውን ጎል አስቆጥሯል ።

የኢታንግ ከተማ ግብ ጠባቂም ማሞ አየለ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ።ጨዋታውም በቦዲቲ ከተማ ሶስት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።


