የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ወንዶ ገነት አሊ ሀብቴ ጋራዥን የጋምቤላው ኑዌር ዞን አሳይታ ወረዳን ከፍፁም የጨዋታ ብልጫ ጋር አሸንፈዋል።
አስቀድሞ ሶስት ላይ የተካሄደው የሲዳማው ተወካይ ወንዶ ገነት እና የድሬ ዳዋ ተወካይ አሊ ሀብቴ ጋርዥ ጨዋታ በሱራፌል ሙሉወርቅ ድንቅ ብቃት ታግዘው ሶስት ለባዶ አሸንፈዋል።
በቀዝቃዛ የአየር ፀባይ የተጀመረው የሁለቱም ጨዋታ እንደ አየሩ አጀማመሩም የቀዘቀዘ ነበር ነገር ግን ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን መመልከት ችለናል ።

በተደጋጋሚ የአሊ ሀብቴ ጋራዥን ጎል በተደጋጋሚ መፈተሽ የጀመሩት ወንዶ ገነቶች በመጨረሻ ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ በሰውነት ጉዬ ቆንጆ ጎል መሪ መሆን ችለዋል ።ከጎሉ በኋላ የተነቃቁት ወንዶ ገነቶች ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርገም ጎል ማስቆጠር ግን አልቻሉም ።የመጀመሪያው አጋማሽም በወንዶ ገነት አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
ከእረፍት እንደተመለሱ አጥቅተው መጫወት የጀመሩት ወንዶ ገነቶች ተቀይሮ በገባው ሱራፌል ሙሉወርቅ በተደጋጋሚ የጎል ማግባት ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም ጎል ማግባት አልቻሉም ።አሊ ሀብቴ ጋራዦችም ቢሆኑ በአጋጣሚ የሚያገኙት የመልሶ ማጥቃት መጠቀም አልቻሉም ነበር ።
ከብዙ ጥረት በኋላ ከቀኝ መስመር የተገኘውን ቅጣት ምት የአሊ ሀብቴ ጋራዥ ተከላካይ በጭንቅላቱ ቢመልሰውም በጨዋታው ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርግ የነበረው ሱራፌል ሙሉወርቅ ድንቅ ጎል አስቆጥሩ የጎል ልዩነቱን ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል።

ጨዋታው ወደ ማለቁ በተቃረበበት ሰዓት ሱራፌል ሙሉወርቅ ከግራ መስመር በመነሳት በግራ እግሩ እጅግ ውብ የሆነች ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በወንዶ ገነት ሶስት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ሱራፌል ሙሉወርቅ ከደጋዎች አድናቆት ሲቸረውም ተመልክተናል።
አምስት ሰዓት ላይ የጀመረው የጋምቤላው ተወካይ ኑዌር ዞን እና የአፋሩ ተወካይ አሳይታ ወረዳ ጨዋታ በኑዌር ዞን የበላይነት ተጠናቋል።
ገና ከጨዋታው ጅማሬ ጀምሮ ረጃጅም ኳሶችን ለአጥቂዎች መላክ የጀመሩት ኑዌር ዞኖች ጎል ለማስቆጠር ብዙም አልተቸገሩም ።በአጋጣሚ ያገኙትን ኳስ ቸንኮት ጆን ወደ ጎልነት ቀይሮታል ።ከጎሉ በኋላ ወደ ጨዋታ ለመመለስ ሲጥሩ የነበሩት አሳይታ ወረዳዎች በተደጋጋሚ ለአጥቂዎች የሚልኩት ኳስ በኑዌር ዞን ተከላካዮች ሲወሰድባቸው ነበር ።

ከእረፍት መልስ ራሳቸውን በሚገባ አጠናክረው የገቡት ኑዌር ዞኖች ጎል ለማስቆጠር ብዙም አልተቸገሩም ።በጨዋታው ግሩም እንቅስቃሴ ሲያሳይ በነበረው ቾል ላም አማካኝነት ሁለተኛ ጎል አስቆጥረዋል ።አሳይታ ወረዳዎች በአንድ ሁለት ቅብብል የኑዌር ወረዳ ተከላካዮችን ለማለፍ የሚያደርጉት ጥረት በተደጋጋሚ ይቆረጥባቸው ነበር ።

ጥቃት መሰንዘራቸውን ያላቆሙት ኑዌር ዞኖች በኪም ላም አማካኝነት ሶስተኛ ጎል ማስቆጠር ችለዋል ።ከጎሏ መቆጠር በኋላ አሳይታ ወረዳዎች ደጋፊውን ያዝናና ጨዋታ ሲጫወቱ ለማየት ችለናል።በጨዋታው ግሩም እንቅስቃሴ በማሳየት ደጋፊውን ያስደሰተው ቾል ላም ግሩም ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በኑዌር ዞን አራት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።



