መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል ሲያገኝ ሦስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል
ሀዲያ ሆሳዕናሽረ ምድረገነትባህርዳር ከተማነጌሌ አርሲኢትዮጵያ መድህንኢትዮጵያ ንግድ ባንክዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማፋሲል ከነማ

ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል ሲያገኝ ሦስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

አጋራ
አጋራ

በአዳማ እና ሀዋሳ በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛው የዕለቱ አሸናፊ ሲሆን ቀሪ ሦስት መርሀ ግብሮች ነጥብ በመጋራት ተቋጭተዋል።

ምድገነት ሽረን ከፋሲል ከነማ ጋር ያገናኘው ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረች ጎል ምድረገነት ሽረዎች አንድ ነጥብን ተጋርተው ወጥተዋል። ፋሲሎች በብዙ ረገድ የተሻሉበት ቢሆንም ጎልን ያስቆጠሩት ግን ከዕረፍት መልስ ነበር። 56ኛው ደቂቃ ላይ ከዳግም አወቀ የቀኝ የሜዳው ክፍል የመጣችን ኳስ በረከት እና ታምራት በጥሩ ስብጥር በፈጠሩት ቅንጅት አዲሱ ፈራሚ ታምራት እያሱ አመቻችቶለት በረከት ግዛው በመጨረሻም አፄዎቹን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።

የጨዋታው ደቂቃ እየገፋ ሲመጣ ፋሲሎች ሦስት ነጥብን የሚያገኙ ቢመስሉም ምድረገነት ሽረ 89ኛው ደቂቃ ላይ ዳንኤል ዳርጌ በግንባር በመግጨት ከመረብ ባዋሀዳት ጎል 1ለ1 በሆነ ውጤት በመጨረሻም ተጠናቋል።

ማምሻውን ድሬዳዋ ከተማን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገናኘው መርሀግብር በሀምራዊ ለባሾቹ አሸናፊነት ተደምድሟል። ጥሩ አጀማመር የነበራቸው ድሬዎች 14ኛው ደቂቃ ላይ የግብ ዘቡ አብዩ ካሳዬ ወደኋላ የተሰጠውን ኳስ በድጋሚ ለቡድን ጓደኞቹ ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ አዲስ ግደይ ቀድሞ ደርሶባት ንግድ ባንክን መሪ ያደረገች ግብን መረቡ ላይ አሳርፏታል። ከዕረፍት መልስ ብርቱካናማዎቹ በማሳደር ንግድ ባንኮች በበኩላቸው አስጠብቀው ለመውጣት በመከላከል አቀራረብ ሲጫወቱ ያስተዋልን ሲሆን 61ኛው ደቂቃም እንደነበራቸው ብልጫ ድሬዳዋ ጎል አግኝቷል።

61ኛው ደቂቃ ከግራው የሜዳው ክፍል ከቅጣት ምት አብዱሰላም የሱፍ ሲያሻማ በሳይመን ፒተር ወደኋላ የተጨረፈን ኳስ መሐመድ ኑርናስር አግኝቶ ቡድኑን ወደ አቻነት አሻግሯል። 66ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታው እንደደረሰ ሳይመን ፒተር ከቀኝ በረጅሙ ወደ ሳጥን የጣለውን ኳስ አዲስ ግደይ ተቆጣጥሮ ወደ ውስጥ ሲያሻግር የድሬዳዋ ተከላካዮች አቋቋም ስህተት ታክሎበት ናትናኤል ዳንኤል በግንባሩ በማስቆጠር ንግድ ባንክ 2ለ1 አሸናፊ ሆኗል።

እጅግ በብዙ ነገር የተቀዛቀዘ የነበረው እና በጠንካራ ፀሐይ ታጅቦ የተደረገው የሀዋሳ ዩኒቨርስቲው የባህርዳር ከተማ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ጎል ሳይቆጠርበት ተጠናቋል። በጨዋታው ከነበሩት በርከት ያሉ ደጋፊዎች እና የዕለቱ ዳኛ ባህሩ ተካ የባህርዳሩ አማካይ ብሩክ ሰሙ ሳጥን ውስጥ ጥፋት ተሰርቶበት የፍፁም ቅጣት ምት ሳይሰጠው የቀረበት አጋጣሚ ብቻ ከጨዋታው ይልቅ የተስተዋሉ ትኩረት ሳቢ ጉዳዮች ነበሩ።

ኢትዮጵያ መድንን ከሀድያ ሆሳዕና ባገናኘው የምሽቱ ጨዋታ በዝናባማ አየር ታጅቦ 1ለ1 ተጠናቋል። አጀማመራቸው ጥሩ ይመስሉ የነበሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች 12ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥረዋል። ፀጋአብ ግዛው የግል ጥረቱን ተጠቅሞ ከቀኝ ሰብሮ ገብቶ ያሻገራትን ኳስ ታሪኩ ፀደቀ በተከታታይ ጨዋታ ጎል በማስቆጠር ቡድኑን ቀዳሚ አድርጓል። 30ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን ምት ብሩክ በላቸው ያሻገረለትን ኳስ አማኑኤል ኤርቦ በግንባር ገጭቶ በማስቆጠር በመጨረሻም በሁለተኛው አጋማሽ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር 1ለ1 ተቋጭቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...