By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ፈረሰኞቹ ድል ሲቀናቸው ጥሩ ፉክክር የነበረው የነገሌ እና ሸገር ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
ዜናዎች ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ቅዱስ ጊዮርጊስአርባምንጭ ከተማየጨዋታ ዘገባሸገር ከተማነጌሌ አርሲየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎች

ፈረሰኞቹ ድል ሲቀናቸው ጥሩ ፉክክር የነበረው የነገሌ እና ሸገር ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

hatricksport team
hatricksport team 3 months ago
Share
SHARE

በስምንተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ድል ሲመለስ ሁለት ቀይ የነበረው የመቻል እና ድሬዳዋ ጨዋታ እንዲሁም አስገራሚ ፉክክር የታየበት የነገሌ እና ሸገር መርሀግብር በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

መቻል 1-1 ድሬዳዋ ከተማ

አዲስ አበባ ስታዲየም በብቸኝነት ዘጠኝ ሰዓት ሲል የጀመረው የመቻል እና ድሬዳዋ ጨዋታ ሁለት ቀይ ካርድ አስመልክቶን በአቻ ውጤት ተጠናቋል። መቻሎች አጀማመራቸው ጥሩ በማድረግ በቀጠሉበት ጨዋታ 30ኛው ደቂቃ ላይ አማካያቸውን ለማጣት ተገደዋል። መናፍ ኢሞሮ የድሬዳዋው አማካይ አቡበከር ሻሚል ላይ በሰራው አደገኛ ጥፋት የዕለቱ ዋና ዳኛ ሀይማኖት አዳነ በቀጥታ ቀይ ካርድ ካስወጡት በኋላ ባሉት ቀሪ ደቂቃዎች የቁጥር ብልጫውን ለመጠቀም ጥረት ያደረጉት ብርቱካናማዎቹ 36ኛው ደቂቃ አቡበከር ሻሚል በጥሩ ዕይታ ያቀበለውን ኳስ መሐመድ ኑርናስር ፍጥነቱን ተጠቅሞ ከመረብ በማሳረፍ የአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን ቡድን መሪ አድርጓል።

በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው ሲመለስ ከዕረፍት በፊት ለመቻሉ አማካይ በቀይ መውጣት ምክንያት የነቀረው አቡበከር ሻሚል በሁለት ቢጫ በሰራው ጥፋት 51ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከወጣ በኋላ መቻሎች ወደ ጨዋታ ለመመለስ በተለይ በዕለቱ ልዩነት ፈጣሪ በነበረው ጋናዊው አጥቂ ኮሊስ ኮፊ አማካኝነት በድግግሞሽ ማጥቃታቸውን በይበልጥ አሳድገዋል። ጎል አስቆጣሪያቸውን መሐመድ ኑርናስርን በጉዳት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሆስፒታል ሸኝተው በተጋጣሚያቸው በእንቅስቃሴ በቀጣዮቹ ደቂቃዎች የተበለጡት ድሬዳዋ ከተማዎች 63ኛው ደቂቃ ከኮሊስ ያገኘው ኳስ አብዱልከሪም ወርቁ ወደ ጎልነት ለውጦ ጨዋታው በመጨረሻም 1ለ1 ተቋጭቷል።

- ማሰታውቂያ -

ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 አርባምንጭ ከተማ

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ፈረሰኞቹን ከአዞዎቹ ያደረጉት መርሀግብር በቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይነት ከድምዳሜ ደርሷል። ተመጣጣኝ የሚባል ነገር ግን ብዙም ሳይነቱ ጎልቶ ባልተስተዋለው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መጠነኛ የማጥቃት ደመነብስን ተላብሰው ሲጫወቱ የተስተዋሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች 43ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥረዋል። ከግራ መስመር በኩል ተገኑ ተሾመ ወደ ውስጥ የላካት ኳስ ተጨራርፋ የደረሰችው ፀጋ ከድር ወደ ጎልነት ለውጧት ቡድኑ መሪ አድርጓቸዋል።

ከዕረፍት ተመልሶ በቀጠለው እና አዞዎቹ የተጫዋች ለውጥን ጭምር አድርገው መጫወት ቢችሉም ቅዱስ ጊዮርጊሶች በተለይ በቢኒያም ፍቅሬ እና ተገኑ ተሾመ አማካኝነት የሚያስቆጩ አጋጣሚዎችን ፈጥረው ይበልጥ የጎል መጠናቸውን ከፍ የሚያደርጉበትን ዕድሎች ቢያገኙም ጨዋታው በመጨረሻም በተቆረጠረችዋ ብቸኛ ጎል ፈረሰኞቹን ከተከታታይ ነጥብ መጣሎች በኋላ 1ለ0 አሸናፊ አድርጋ ተጠናቋል።

ነገሌ አርሲ 2-2 ሸገር ከተማ

እጅግ አስገራሚ የሜዳ ላይ ፉክክር እና የአራት ጎሎች ድራማን ያሳየን የምሽቱ የኦሮሚያ ደርቢ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተቋጭቷል። በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ማኑሄ ወልደፃዲቅ እየተመራ አመሻሹን በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሜዳ የተደረገው ጨዋታ በመጀመሪያው አርባ አምስት ከፉክክር አንፃር መጠነኛ መልክ ቢኖረውም በአንፃራዊነት ነገሌ አርሲዎች በፈጣን ሽግግር የተሻሉበት ሸገሮች በበኩላቸው ወጥ ባይሆነም በጥልቅ እንቅስቃሴ መጫወት መርጠው የተስተዋሉበት ነበር።

ከመጀመሪያው አጋማሽ ይልቅ ከፍተኛ መሻሻሎችን ይዞ የተመለሰው ከ አስደናቂ የሜዳ ላይ ግለቶችንም ያሳየን ሁለተኛው አጋማሽ ሸገር ከተማዎች አሳድገው የተመለሱን የመስመር አጨዋወት ጫና በሚፈጥር እንቅስቃሴ ተጋጣሚያቸው ላይ ጎል አስቆጥረዋል። 55ኛው ደቂቃ ላይ ናትናኤል ዘለቀ በአግባቡ ያቀበለው ኳስ ከሳጥኑ የግራ ክፍል ሆኖ ያገኘው ጀቤሳ ሜኤሳ የተከላካዮች ዝንጉነት ታክሎበት የቀድሞው ክለቡ ላይ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን መሪ ሲያደርግ ደስታውን ሳይገልፅ ቀርቷል። ጨዋታው ቀጥሎ 70ኛው ደቂቃ ላይ እንደደረሰ የአሚር አብዶ ጥሩ ዕይታ ታክሎ ጀቤሳ ሜኤሳ በድጋሚ ጎል በማስቆጠር ለራሱም ለቡድኑም ሁለተኛ ጎል አድርጓታል።

ሁለት ጎሎች ካስተናገዱ በኋላ የተጫዋቾችን ለውጥ በማድረግ ልማደኛውን የመስመር አጥቂ ከቤ ብዙነህን መነሻ የማጥቃት ምንጫቸው አድርገው የታዩት ነገሌዎች 75ኛው ደቂቃ ምስጋናው መላኩ አቀብሎት ግሩም ጎል ከቤ ብዙነህ ከመረብ አዋህዶ ቡድኑን ወደ ጨዋቻ ጨዋታ መልሷል። መደበኛው የጨዋታ ደቂቃ ተጠናቆ በጭማሪው ሰባት ደቂቃ ውስጥ ከሳጥኑ ጠርዝ 90+2 ላይ የተገኘን የቅጣት ምት ሮሆቦት ሰለሎ የባህሩ ነጋሽ የንቃት ጉድለት ታክሎበት በቀጥታ የመታት ኳስ ከመረብ አርፋ በመጨረሻም በበርካታ ደጋፊዎች ፊት የተደረገው ጨዋታ 2ለ2 ተፈፅሟል።

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By hatricksport team
Follow:
Hatricksport team
Previous Article ሲዳማ ቡና የሊግ መሪነቱን ሲያጠናክር ምድረ ገነት ሽረ እና ኢትዮጵያ ቡናም አሸንፈዋል
Next Article የ8ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችሀዲያ ሆሳዕናየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህንሻሸመኔ ከተማ

በ27ተኛዉ ሳምንት የሊጉ የመዝጊያ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ እና ኢትዮጵያ መድን ማሸነፍ ችለዋል !!

Ermias Misganaw By Ermias Misganaw 2 years ago
የዋልያዎቹ አሰላለፍ ይፋ ሆናል
“ቅ/ጊዮርጊስ ዋንጫ ማንሳቱ ላይ ተስፋ አይቆርጥም፤ የደርቢ ጨዋታውንም ያሸንፋል” ሄኖክ አዱኛ /ቅ/ጊዮርጊስ/
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ አላቀረበችም”አቶ ባህሩ ጥላሁን 
የጨዋታ ዘገባ |የምንይሉ ወንድሙ ብቸኛ ግብ መቻልን ባለድል አድርጋለች !!
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?