By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ሲዳማ ቡና የሊግ መሪነቱን ሲያጠናክር ምድረ ገነት ሽረ እና ኢትዮጵያ ቡናም አሸንፈዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የጨዋታ ዘገባሽረ ምድረገነትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችሀዋሳ ከተማኢትዮጵያ ንግድ ባንክሲዳማ ቡናሀዲያ ሆሳዕና

ሲዳማ ቡና የሊግ መሪነቱን ሲያጠናክር ምድረ ገነት ሽረ እና ኢትዮጵያ ቡናም አሸንፈዋል

hatricksport team
hatricksport team 3 months ago
Share
SHARE

በተመሳሳይ አንድ አንድ ጎል የተቆጠረባቸው ሦስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቀዋል።

ምድረ ገነት ሽረ 1-0 ሀዋሳ ከተማ

ከቀትር መልስ የአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው የምድረ ገነት ሽረ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታው በሰሞነኛ አቋማቸው በተሻለ ቁመና ላይ በሚገኙት ሽረዎች አሸናፊነት ተጠናቋል። በመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ተመጣጣኝ በሚመስለው የቡድኖቹ ጨዋታ 34ኛው ደቂቃ ተካልኝ ደጀኔ ያሻገራትን ኳስ የግብ ዘቡ ሰይድ ሀብታሙ በአግባቡ አለመቆጣጠሩን ተከትሎ ኳሷን ያገኘው አቤል ማሙሽ ወደ ጎልነት ለውጦ ቡድኑን ቀዳሚ አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ በእንቅስቃሴ መሻሻል ምድረ ገነት ሽረዎች ደግሞ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ነጥብ ይዞ ለመውጣት ጥረት ያደረጉበት ሁለተኛው አጋማሽ ሀዋሳዎች ጎል አስቆጥረው አወዛጋቢ በሆነ የዳኛ ውሳኔ የተሻረበት እና መደበኛው የጨዋታ ደቂቃ ተጠናቆ የተሰጠው ጭማሪ ሳያልቅ የዕለቱ ዋና ዳኛ አሸብር ሰቦቃ ፊሽካቸውን ያሰሙበትን ውዝግቦችን ብናስተውል ጨዋታው በመጨረሻም በምድረ ገነት ሽረ 1ለ0 አሸናፊነት ተደምድሟል።

- ማሰታውቂያ -

ሲዳማ ቡና 1-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የሲዳማ ቡና ፍፁማዊ የእንቅስቃሴም ሆነ የሙከራ የበላይነት ከፍ ብሎ በታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ ጎል የተቆጠረው ገና በመጀመሪያው ደቂቃ ነበር። 4ኛው ደቂቃ ላይ ከሬድዋን ናስር የመጣለትን ኳስ ተከላካዩ ብርሀኑ በቀለ በግንባር ገጭቶ ፓላክ ቾል መረብ ላይ በማሳረፍ ቡናማዎቹን ቀዳሚ አድርጓቸዋል።

ከዕረፍት መልስ የተጫዋች ለውጥን በማድረግ የአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገዱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ጨዋታ ለመመለስ ጥረት ባደረገበት እና ሲዳማ ቡናዎች በበኩላቸው ለኋላ ክፍላቸው መጠነኛ ጥንቃቄን በመውሰድ ማጥቃቱ ላይ ለተጨማሪ ጎል መጫወት የቻሉ ቢሆንም የዕለቱ ዳኛ ዳንኤል ይታገሱ ንግድ ባንኮች በሳይመን ፒተር አማካኝነት ጎል አስቆጥረው መስመር አላለፈች በሚል ከተሻረችዋ ክስተት በኋላ ጨዋታው ሲዳማ ቡናን 1ለ0 አሸናፊ አድርጎ ሲጠናቀቅ ቡድኑም ሊጉን መምራቱን አጠናክሮ ቀጥሏል

ኢትዮጵያ ቡና 1-0 ሀድያ ሆሳዕና

ቡናማዎቹ በሀያ ደቂቃዎች ውስጥ በይበልጥ ከመስመር መነሳትን መርጠው ለመጫወት በጣሩበት ወቅት 11ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥረዋል። ሚኪያስ በዳሶ ወደ ጎል የመታትን ኳስ የሀድያ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ሳጥን ውስጥ ኳስን በእጅ በመንካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ናይጄሪያዊው አጥቂ አቡበከር አዳሙ ወደ ጎልነት ለውጦ ቡድኑን መሪ እንዲሆን አስችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ የተጫዋች ለውጥን ከማድረጋቸው ባለፈ የአጥቂ ክፍላቸውን በማብዛት ወደ ጨዋታ ቅኝት በይበልጥ የገቡት እና በርካታ አጋጣሚዎችን የፈጠሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ቢሆንም የመጨረሻው ሜዳ ላይ ያሳዩ በነበሩት ደካማ የአፈፃፀም ጉድለት የተነሳ ከዕረፍት በፊት በተቆጠረባቸው ጎል ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By hatricksport team
Follow:
Hatricksport team
Previous Article መቐለ 70 እንደርታ ሶስት ጨዋታ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆን ሲወሰን በተጨማሪም ሀያ ሺ ብር ቅጣት ተጥሎበታል!!
Next Article ፈረሰኞቹ ድል ሲቀናቸው ጥሩ ፉክክር የነበረው የነገሌ እና ሸገር ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንዜናዎችዋልያዎቹ

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውላቸውን አራዘሙ

hatricksport team By hatricksport team 3 years ago
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴቶች እግርኳስ ላይ መንገሱን አወጀ….
“የተደበቀ እጅ ሊኖር ይችላል እንጂ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ይህን ቀጥቶኛል ብዬ ለማመን ይከብደኛል”
ሪፖርት | በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ 3ነጥቡን ማስመዝገብ ችሏል።
“በደብዳቤ ጋጋታ አልበረግግም፤ የወከሉኝን የሙያ ጓደኞቼን መብት ለማስከበር እስከመጨረሻው እታገላለሁ”አቶ ሰለሞን አባተ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?