መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ ቡና ፊፋ ያዘዘውን ትዕዛዝ ፈፀመ
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችፊፋ

ኢትዮጵያ ቡና ፊፋ ያዘዘውን ትዕዛዝ ፈፀመ

አጋራ
አጋራ

አለም አቀፉ የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፊፋ ኢትዮጵያ ቡና የዑጋንዳዊውን ቦገን የ6 ወር ደመወዝ እንዲከፍል የሰጠው ውሣኔ ተግባራዊ ሆነ፡፡

ጋናዊው ተጨዋች ለፊፋ ያቀረበው ክስ ተግባራዊ መሆኑ የግድ ቢሆንም ተጨዋቹ የሄደበት መንገድ ለኢትዮጵያ ቡና ዋና ስራ አስኪያጅ ለአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የተዋጠ አልሆነም፡፡ አቶ ገዛኸኘ ለሀትሪክ ሲናገሩ “በፍፁም ተገቢ አካሄድ አይደለም ለዲሲፕሊን ኮሚቴ ሳያሳውቅ በቀጥታ ለፊፋ መክሰሱ ተገቢ አልነበረም፤ ነገር ግን ጉዳዩን ወደ ፊፋ ለመውሰድ የሄድንበት ጊዜ ይግባኝ የማቅረቢያውን ቀነ ገደብ በማለፉ መሸነፋችንና የተባለውን ገንዝብ መክፈላችን የግድ ሆኗል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ፊፋ ክለቡ የተጨዋቹን ደመወዝ እስኪከፈል ድረስ በሚል የኢትዮጵያ ቡና የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ተጨዋቾች ዝውውርን በማገድ የቆየ ሲሆን ክለቡ ለተጨዋቹ በውሉ መሠረት ገንዘቡን ከከፈለ በኋላ ግን የዝውውር እገዳው መነሳቱ ታውቋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...