ሊግ ካምፓኒና ዲ ኤስ ቲቪ የፊታችን አርብ ይፈራረማሉ!

 

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ዲ ኤስ ቲቪና የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ካምፓኒ የውል ስምምነታቸውን የፊታችን አርብ በሸራተን አዲስ ይፈራረማሉ፡፡

አርብ ከቀኑ 11.30 የሚካሄደው የፊርማ ስነስርአት ላይ የመንግስት ባለስልጣናት የሚዲያ ሰዎች ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች የሚገኙ ሲሆን በዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቀጣዮቹ 5 አመታት ዲ ኤስ ቲቪ 22.5 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ከሊግ ካምፓኒው ጋር መስማማታቸው ይታወቃል፡፡

አንዳንድ ወገኖች ደግሞ ዲ ኤስ ቲቪ ያሸነፈው በ 68 ሚሊየን ዶላር ነው የሚል በመሆኑ በአርቡ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ሁሉም እውነት ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport