አፄዎቹ ዋንጫ የሚቀበሉበት ቀን ታውቋል !

የ2013 የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ መሆናቸውን ያረጋገጡት ፋሲል ከነማዎች ዋንጫውን የሚያነሱበት ቀን ታውቋል ።

ፋሲል ከነማ አስቀድሞ ሚያዚያ 30 እንደሚያነሱ ቢገለፅም በነበረ መጠነኛ የዝግጅት እጥረት ምክንያት ለግንቦት 8 መራዘሙ የሚታወስ ነው ።

ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው መረጃ መሰረት አፄዎቹ በዚህ ሳምንት ከ ድሬደዋ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ባለሜዳ አለመሆናቸውን ተከትሎ ዋንጫው ለማንሳት ለቀናት መገፋቱ ታውቋል ።

በዚህም መሰረት አፄዎቹ ታሪካዊውን ዋንጫቸውን በቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 14/2013 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ከ ሐዋሳ ከተማ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ከፍ አድርገው እንደሚያነሱ ለማወቅ ተችሏል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor