በዛሬው ዕለት በ ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል የዋልያዎቹን ከ ስምንት ዓመታት በኋላ ማለፋቸውን ተከትሎ በዛሬው ዕለት የብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ክፍል ጨምሮ የቀድሞው ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።
በፓናል ውይይት ላይ ከተነሱ ሀሳቦች መካከል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተዋል ።
” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማዳጋስካርን በ ባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ባሸነፍንበት ጨዋታ የ 4,000 ዶላር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተቀጥቷል ” ሲሉ በውይይቱ ላይ ገልፀዋል ።
ለቅጣቱ ዋነኛ መንስዔ ሆኖ የተገለፀው የባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም የመቀመጫ ወንበር ፣ የሚዲያ ስፍራ እና ተያያዥ ቦታዎች ደረጃቸውን ያላሟሉ መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ ገልፀዋል ።
- ማሰታውቂያ -
አቶ ባህሩ ጥላሁን በውይይቱ በተጨማሪም ባነሱት ሀሳብ ” ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመንግስት ድጋፍ ይደረግላቸዋል ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከስፖንሰሮች አልፎ አልፎ ከሚያገኘው፣ ከ የካፍ እና ፊፋ ከሚላኩ ገንዘቦች ውጪ ከመንግስት ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ አይደረግለትም ” ሲሉ ተናግረዋል ።