የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ከሃዋሳ ወደ አዲስ አበባ ተዛወረ….

 

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ እየተካሄደ ሲሆን የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ጠቅላላ የኢትዮጲያ  የቱሪስት ከተማ ተብላ በምትጠራው በሃዋሳ ከተማ የዛሬ ሳምንት ሊካሄድ ቀጠሮ ቢይዝም የቦታ ለውጥ ማድረጉ ታውቋል፡፡በዚህም ሀዋሳ የነበረው ጠቅላላ ጉባኤ ወደ አዲስ አበባ ከተማ መዛወሩ ታውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ለተሰብሳቢው በላከው ደብዳቤ ሀገሪቷ ካለችበት የጸጥታ ችግር አንጻር ወደ አዲስ አበባ መዞሩ ታውቋል፡ በቀጣይ ቀናቶች እሁድ የሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ቦታን ፌዴሬሽኑ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport