ኢትዮጵያዊያን ዳኞች በሴካፋው ይጠበቃሉ !

 

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄደው የሴካፋ ከ 20 ዓመት በታች ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊያኖቹ ዳኞች ጨዋታዎችን እንደሚመሩ ይጠበቃል ።

ውድድሩ በዛሬው ዕለት አንድ ብሎ ሲጀምር አስተናጋጅ ሀገሯ ታንዛኒያ ጅቡቲን ስታስተናግድ ኢትዮጵያዊያኖቹ በላቸው ትግሌ በሁለተኛ ረዳት ዳኛ እንዲሁም በላይ አስረስ በአራተኛ ዳኝነት ጨዋታውን እንደሚመሩት ይጠበቃል ።

በተመስገን ዳና የሚመራው የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ ኬንያ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor