የመቐለ 70 እንደርታ ተጨማሪ 4 ተጨዋቾች አዲስ አበባ ገብተዋልበመከላከያ ሰራዊት በተጀመረው ህግ የማስከበር ርምጃ የአየርና የየብስ ጉዞ ቢከለከልም ተጨማሪ 4 የመቀለ 70 እንደርታ ተጨዋቾች በሰመራ አድርገው አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ምንተስኖት ከበደ…ሰለሞን ሀብቴ…አወል አብደላና ተስፋዬ በቀለ እንዲሁም ከመቀለ 70 እንደርታ ወልዋሎን የተቀላቀለው ዳንኤል ደምሴ አዲስ አበባ መግባታቸው ተረጋግጧል፡፡
ዳንኤል ደምሴ መቐለ ከደረሰ በኋላ ወደ አዲግራት ሳይጓዝ በመቅረቱ ከመቐለ የመመለስ ዕድል አግኝቷል፡፡
ይህም ወደ አዲስ አበባ የመጡትን ተጨዋቾች ቁጥር 10 አድርሶታል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport