አዲስ አበባ ኢንጂነር ሃ/የሱስን መረጠች

 

 

ኢንጂነር ሃ/የሱስ ፍሰሃና አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ በቀጣዮቹ 4 አመታት የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንን እንዲመሩ በጠቅላላ ጉባኤ ተመርጠዋል፡፡

ለፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት ኢንጂነር ሃይለየሱስና ኢንስፔክተር የኔነህ ሲሆኑ በጠቅላላ ጉባኤው ከተሰጠ 58 ድምጽ ኢንጂነሩ 44 ድምጽ ሲያገኙ .ኢንስፔክተሩ ደግሞ በ14 ድምጽ ተመርጠዋል፡፡አስገራሚው ነገር ኢንጂነሩን ዕጩ አድርገው ያቀረቡት ቦሌ ክፍለ ከተማዎች በምርጫው ጊዜ አለመኖራቸው ነው
ኢንጂነሩ ከምርጫ በኋላ እንደተናገሩት “በመመረጤ ተደስቻለሁ በቀጣይ ከሚመረጡት አመራሮች ጋር በጋራ ለከተማው እግር ኳስ ለመስራት ተዘጋጅቻለሁ” በማለት ገልጸዋል፡፡
በዚሁ ምርጫ በስራ አስፈጻሚነት የተወዳዳሩት አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ከ19 ተወዳዳሪዎች መሃል በአንደኝነት የተመረጡ ሲሆን ባገኙት 42 ድምፅ መሠረት በቀጣዮቹ 4 አመታት ፌዴሬሽኑን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡

በምርጫው መሠረት ከኢንጂነር ሃ/የሱስ ፍሰሃ ውጪ ስምንቱ አዳዲስ ሰዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የምርጫ ዕጩ ማቅረቢያ ቀኑ ቢያልፍም ማህበራት ማደራጃና ስፖርት ኮሚሽን ከምርጫው መስፈርት ውጪ ሴቶችን ለማስመረጥ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ከምርጫው መስፈርት መሃል አንዱ በሆነው 30% ሴቶች ይሁኑ የሚለው ክለቦችና ክፍለ ከተሞች አለማቅረባቸው ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ የደንብ ማፀደቂያ ውይይት ላይም ሴቶች 30% መሆን አለባቸው በሚል ቢስማሙም ገዢ ወይም አስገዳጅ መሆን የለበትም በሚለው መወሰኑ ታውቋል፡፡

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *