ኢትዮ ኤሌክትሪክ የዕገዳ ደብዳቤ ወጥቶበታል

 

ቀሪ የ6 ወር ኮንትራቴ ደመወዝ አልተከፈለኝም በሚል በታፈሰ ተስፋዬ የተከሰሰው ኢትዮኤሌክትሪክ ላይ ዛሬ የዕገዳ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡ የዲሲፕሊንና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎች ክለቡ የተጨዋቹን የ6 ወር ደመወዝ እንዲከፍል በመወሰናቸው ክፍያው ካልተፈጸመ ምንም አይነት ግልጋሎት እንደማያገኙ ተወስኗል፡፡ ይህም አዲስ ለተሾመው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ሌላ ራስ ምታት ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል፡፡

በውሳኔው ዙሪያ የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ለማ ደበሌ ግን “በፍጹም አንከፍልም አታስፈርሙም ከተባልን ለፌዴሬሽኑና ለካስ አቤት አንልም የህግ ክፍል አለን በቀጥታ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት እንወስደዋለን” በማለት ተናግረዋል፡፡እግርኳሳዊ ጉዳዮችን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት መውሰድ በፊፋና በካፍ የተከለከለ በመሆኑ ክለቡ ላይ ሌላ ርምጃ እንዳይወሰድ ተሰግቷል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport