ኢትዮጲያ መድን ኢንስትራክተር ይግዛው ብዙአየሁን ቀጠረ

ኢትዮጲያ መድን ከቦታቸው በተነሱት አቶ ፍሰሃ ቦታ ኢንስትራክተር ይግዛው ብዙአየሁን አዲሱ ዋና ስራ አስኪያጅ አድርጎ ቀጥሯል፡፡
ኢንስትራክተሩ በዳኝነት ረዘም ላለ ጊዜ የሰሩ ሲሆን ኢንተርናሽናል አርቢትር ሆነውም ሀገሪቱን ወክለዋል፡፡

ለበርካታ ዳኞች ስልጠና በመስጠት የዕውቀት ሽግግር ያደረጉ ሲሆኑ የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሃፊ ሆነውም አገልግለዋል በካፍ እየተከፈላቸውም ትምህርትና ስልጠና ላይ የአገራቸውን ባለሙያዎች የማብቃት ስራ የሰሩ ባለሙያ ናቸው፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport