መቐለ 70 እንደርታን በሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ለማድረግ እየተሞከረ ነው…

 

በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሚሆነው የመቐለ 7 እንደርታን 4 ተጨዋቾችን ወደ አዲስ አበባ በማምጣት ክለቡን በውድድሩ ላይ እንዲቀጥል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ከዚህ መረጃ ጀርባ ካለው ምንጫችን በተገኘ መረጃ አራቱን ተጨዋቾች በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት የተነሳ እስከ ሀሙስ እንደ 11ዱ ጓደኞቻቸው ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ከሆነ የካፍ ኤ ላይሰንስ ያለው አሰልጣኝ በጊዜያዊነት እንዲይዘው ተደርጎ አርብ ምሽት ወይም ቅዳሜ ጠዋት ካይሮ ለመብረር መታሰቡ ታውቋል፡፡

የመቐለ 70 እንደርታ ተጋጣሚ የሆነው የሊቢያው ክለብ ትሪፖሊ ላይ ጨዋታ ማድረግ ስለማይችል ቱኒዝ ላይ ይጫወትበት የነበረው ሜዳ ፋሲል ከነማ አርብ ምሽት የሚጫወትበት በመሆኑ በኤን ፒፒ አይ ሜዳ ጨዋታውን ለማድረግ መምረጡ ታውቋል፡፡ ከካፍና ከሊቢያው ክለብ ጋር ያለውን የመረጃ ልውውጥ የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሃላፊነት እየተወጣ መሆኑ ታውቋል፡፡

አሁንም ግን የጉዞው ወጪ ከየት እንደሚመጣ የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን የካይሮ የቆይታ ሙሉ ወጪን ግን የሊቢያው ክለብ እንዲሸፍንና ከአንድ ሳምንት በኋላ በሚኖረው የመልስ ጨዋታ ላይ መቐለ 70 እንደርታ እንዲሸፍን ለማድረግ እየተሞከረ መሆኑ ታውቋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport