ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ በፊፋ ተመርጣለች

 

አውስትራሊያና ኒውዚላንድ በጋራ ለሚያዘጋጁት ለ2023 የሴቶች የአለም ዋንጫ ከአፍሪካ ሊዲያን ጨምሮ 8 የመሃል ዳኞችና 11 ረዳት ዳኞች መመረጣቸውን ካፍ አሳውቋል፡፡ ከመላው አለም 156 ዋናና ረዳት ዳኞች የተመረጡ ሲሆን ከሚወስዱት ልምምድና ስልጠና በኋላ የአለም ዋንጫው ዳኞች ይታወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአርቢትር ሊዲያ በሻምፒዮናው ላይ ከተሳተፈች 3ኛዋ ሲሆን ከዚህ በፊት በካናዳና ፈረንሳይ በተካሄዱ የሴቶች የአለም ዋንጫ ላይ መዳኘቷ ይታወሳል፡፡ ካፍ ቀኑን ካላራዘመ በስቀር በጥር ወር በሚካሄደው የቻን ውድድር ላይም እንድትመራ ተመርጣለች፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport