ከጥቂት ቀናት በኋላ በ ታንዛኒያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ከ 20 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ኢትዮጵያ በምድብ ሶስት ከ ሱዳን እና ኬንያ ጋር መደልደሏ ይታወሳል ።
ይህንንም ተከትሎ ሴካፋ የውድድሩን የመርሐ ግብር ቀናቶች ይፋ ሲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡድን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከ ሰባት ቀናት በኋላ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።
ይህንንም ተከትሎ :-
- ማሰታውቂያ -
ህዳር 14 :- ኢትዮጵያ ከ ኬንያ
ህዳር 16 :- ኢትዮጵያ ከ ሱዳን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል ።
የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ተመስገና ዳና እየተመሩ ልምምድ መስራት ከጀመሩ ሲሰነባብቱ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አካሂደው ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው ።