ኢትዮጵያን የምትገጥመው ሴኔጋል ስብስቧን አሳውቃለች።

ለ2027ቱ የኬኒያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከሞዛምቢክ እና ኢትዮጵያ ጋር በወዳጅነት ጨዋታ ደግሞ ከኮሞሮስ ጋር የምታከናውነው ሴኔጋል በቀድሞው የአርሰናል እና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ፓትሪክ ቬዬራ እየተመራች ለምታደርጋቸው ጨዋታዎች ለ29 ተጫዋቾች ጥሪን አድርጋለች።
በአውሮፓ እና በኤዥያ ስ
የሚጫወቱ በርካታ ተጫዋቾች በተካተቱበት በዚህ ስብስብ ውስጥ የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ የወቅቱ የአልናስር አጥቂ ሳዲዮ ማኔ በጉዳት እና የሳውዲ ሊግ የአመቱ ምርጥ የግብ ዘብ ተብሎ በተጠናቀቀው አመት የተመረጠው የቀድሞው የቼልሲ ግብ ጠባቂ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን በማግለሉ መካተት ሳይችሉ ቀርተዋል።

ኢትዮጵያን የምትገጥመዋ ሌላኛዋ ሀገር ሱዳን በአሰልጣኝ ኩዋሲ አፕያ መሪነት ከቀናት በፊት ስብስቧኖ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።
ዋልዎቹ ሱዳንን እና ሴኔጋልን መስከረም 15 እና 19 ይገጥማሉ።
አስተያየት ይስጡ