አቅም ካለን ልናሸንፍ እችላለን”
“እኔ ሚዲያውን አልጠራሁም ፌድሬሽኑን ጠይቁ”
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
የ40 ቀናት ዝግጅትን አቀድሞ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን እና ሴኔጋል ጋር ጨዋታ ያለበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መግለጫ ሰጥተዋል።

የቡድናቸው የታክቲክ ጉዳይ በተመለከተ ከጋዝጠኞች ጥያቄ የተነሳላቸው አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ “እንደ ብሔራዊ ቡድን አላማዬ ማሸነፍ ብቻ ነው። ብሔራዊ ቡድን ላይ በአምስት እና ስድስት ቀናት ባህል መመስረት አንችልም። ይሄንን ማድረግ የሚቻለው በክለብ ደረጃ ብቻ ነው” በማለት ተናግረዋል።
በመግለጫው አብዛኛውን ደቂቃ ከሚዲያ ጋር አሰልጣኙ ስለገቡበት ሰጣገባ ሲናገሩ “እኔ እና ሚዲያውን የሚያገናኘን መርህ መኖር አለበት እኔም የሚዲያ አካል ነኝ ዮሐንስ ሳህሌ አደለም ሚዲያውን የጠራው የቀጠራችሁን ፌድሬሽኑን ጠይቁ ልምምዶች ሚስጥር ስለሆኑ መታየት የለባቸውም ይሄ ደግሞ የፊፋ እና የካፍ ህግ ነው”።
አሠልጣኙ አክለውም በሌላ ሀሳባቸው “አቅም ካለን ልናሸንፍ እችላለን። ግን ከኛ የተሻሉ ካሉ ልንሸነፍ እንችላለን። የኛ ዋነኛ አላማ እና ፍላጎት ግን ማሸነፍ ብቻ ነው። ብሔራዊ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ በስምምነታችን ውስጥ ተካቷል “ሲሉ ተደምጠዋል።
40 ተጨዋቾችን ይዘን ዝግጅታችንን ለመጀመር አስበን ነበር ያሉት አሠልጣኙ ግን በክለቦች አህጉር አቀፍ ውድድሮች ምክንያት ከነሐሴ ስምንት ጀምሮ ዝግጅታችንን የጀመርነው 28 ተጨዋቾች ይዘን ነው ብለዋል።
ዋሊያዎቹ በዝግጅታቸው መጀመሪያ ያደረጉት የአካል ብቃት አሠልጣኝ በማምጣት ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ለማወቅ ጥረት መደረጉን አሠልጣኙ ያነሱ ሲሆን በቆይታቸው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና የወጣት ብሔራዊ ቡድኑ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።
አሠልጣኙ አሁን ላይ 23 ተጨዋቾች እንዳሏቸው ገልፀው የወዳጅነት ጨዋታዎችን ተመርኩዘው ተጨዋቾችን ሲቀንሱ ወቅታዊ ብቃትን በመመልከት ተጨማሪ ተጨዋቾችን ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል እንደቻሉ አሳውቀዋል።
ከመጀመሪያ ተጋጣሚያቸው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን አጨዋወት ጋር በተያያዘ ጥያቄ የቀረበላቸው አሠልጣኙ ካየናቸው ነገር አንፃር የሱዳን ብሔራዊ ቡድን በክንፍ የሚጫወት ፣ ተሻጋሪ ኳሶችን የሚያበዛ ፣ ከራሱ ሜዳ በፍጥነት ለመውጣት የሚሞክር ቡድን ነው ግን አሁን ላይ ተቀይሮ ሊሆን ይችላል በማለት መልሰዋል።
አስተያየት ይስጡ