የዋልያዎቹ ጋዜጣዊ መግለጫ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ ከደቂቃዎች በፊት በፌዴሬሽኑ ፅ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል ፡፡

የፌዴሬሽኑ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዳሳወቁት የነገውን ጨዋታ ከሰባ ያልበለጡ ታዳሚያን ብቻ እንደሚመለከቱት ገልፀዋል ፡፡ ይህንንም ተከትሎም ከሚዲያ ተቋማት የተመረጡ ሀያ ባለሙያዎች ብቻ እንዲሁም ሀምሳ የ ቪ አይ ፒ ሰዎች ጨዋታውን እንደሚታደሙ ተገልፆል ፡፡

በመግለጫው ተያይዞ ሲገለፅም ካፍ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታው እንዲደረግ ሲፈቅድ 20 % የስታዲየም ተመልካች እንዲገባ በፌዴሬሽኑ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ገልፀዋል ፡፡

ከአዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት ጋር ተያይዞ አቶ ባህሩ ጥላሁን በሰጡት አስተያየት “የአዲስ አበባ ስታዲየምን ለማደስ ብናስብ እንኳ አቅሙም የለንም የዕድሳት ሃላፊነቱ የስፖርት ኮሚሽኑ ነው፡፡ የስታዲየሙ ባለቤት ስፖርት ኮሚሽን ሲሆን ሜዳውን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትራኩን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያስተዳድሩታል ” ሲሉ በጉዳዩ ላይ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል ፡፡

በነገው ዕለት የሚካሄደው ጨዋታ የቀጥታ ስርጭት ሽፋንን እንደማያገኝ በመግለጫው ላይ ይፋ ተድርጓል ፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor