” ስንሸልማቸው ስንደግስላቸው የኖሩት ሃይሌና ገዛኧኝ ገንዘብ እየባከነ ነው ሽልማቱ ለፓሪሱ ጀግኖች አይገባቸውም ማለታቸው ያሳዝናል”
ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
/ የኢት. ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት/
“ወደ ፓሪስ የሄድነው የተቀመጠ ሜዳሊያ ለማምጣት ሳይሆን በውድድር አሸንፈን ለማግኘት ነው”
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ
// የኢት .አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት /
የአቴሌቶችና አሰልጣኞች ችግርን ለማስወገድ ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ የሚገኙበት የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት እንደሚጥር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ።
- ማሰታውቂያ -
ትላንት ምሽት በማሪዮት ሆቴል በተካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ አሸናፊ አትሌቶችና አሰልጣኞች በተካሄደ የሽልማትና የዕውቅና ስነስርዓት ላይ የኮሚቴው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እንደተናገሩት እየተንከባለለ የመጣውን ችግር መንግስት የማስወገድ ሙሉ ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል።
” ክቡር ጠ/ሚ ባሉበት የአትሌቶችና የየአሰልጣኞችን ችግር እንዲያዳምጡ ችግሩም እንዲፈታ ለማድረግ የምንችለውን እናደርጋለን አይዟችሁ መንግስት ከጎናችሁ ሆኖ ሁሉን ችግሮ ይፈታል ብለን እናምናለለን ኢትዮጵያን ከችግር ለማውጣት ተነሱ የናንተ ጥቅም ሁለተኛ ጉዳይ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ ” ለግለሰቦች መስጠት ቢቸግረንም አትሌቶችና አሰልጣኞች በጋራ ሆነው ከመጡ ውጪ ያገኙትን ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግ ከፈለጉ ቦታ እንሰጣለን ብለው ቃል ገብተዋል ለዚህም ለክቡር ጠ/ሚ ከፍ ያለ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል” በማለት ተናግረዋል።
የኦሎምፒክ ኮሚቴ እንደገና በይግባኝ መታገዱን ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ነው ያሉት ዶክተር አሸብር ”
ስንሸልማቸው ስንደግስላቸው የኖርነው
ጀግኖች አትሌቶቻችን ሃይሌና ገዛኧኝ ለፓሪስ ጀግኖች አትሌቶችና አሰልጣኞች ሽልማት በምንሰጥበት ሰአት ገንዘብ እየባከነ ነው ሽልማት አይገባቸውም በሚል አካውንቱን እንደገና አሳግደውታል በተለይ ሃይሌ ከመሰለ ሲሸለም ከኖረ አትሌት ይሄ ድርጊት መፈጸሙ አይገባም እነሱ ሲያሳግዱ እኛ ስናስነሳ ቆይተናል አሁንም በዚህ ደረጄ አይቸግርም እንወጣዋለን ካለማወቅ የሚመጡ ቀላል ፈተናዎችን እንወጣለን ቲማችን ጠንካራ ነው አዲሱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስራ ከጀመረበት ከነሀሴ 13 ጀምሮ ደራርቱና ህይወት ከመጨመራቸው ውጪ ሁሉም በጋራ የሚሰራ የሚተዋወቅ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስለ ፓሪስ ኦሎምፒክ ደከም ያለ ውጤት የተናገሩት ዶክተር አሸብር የተለመደው ውጤት ከራቀን ቆይቷል በፓሪስ ህዝቡ የጠበቀውን አላገኘም ብሄራዊ ቡድኑ ከተበተነና ግሎባል ማርኬቱ ኢትዮጵያም ሆነ አለም ላይ ተጽዕኖ መፍጠር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ እየወረደ ነው ለተሻለ ድል የተሻለ ጠንካራ ስራ ያስፈልገዋል” ሲሉ አስረድተዋል።
” ዛሬ ለሽልማት እንደተገናኘን በቀጣየይ ስለ ፓሪስ ኦሎምፒክ ጠንካራ ደካማ ጎን ለመምከር ውይይት ተዘጋጅቷል ተገናኝተን ችግሮቻችን ለይተን አውቀን ፈተናዎቻትንን አውቀን ወደፊት የምንጓዝበትን መንገድ መፈጠር አለበት” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “እንደ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ስለ ፓሪስ እያሰብን አይደለም አሁን የምናስበው ስለ ሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር አሸብር ለተሸላሚዎቹ እንደገለጹት የዛሬ ማበረታቻ እናንተን የሚመጥን አይደለም ገንዘቡ ሳይሆን ዋናው ክብሩ ነውና ሽልማቱ እንደምናስባችሁ እንደምናስታውሳችሁ ለመግለጽ ነው” ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተዋል።
በዚሁ የማሪዮት ሆቴል መርሃግብር ላይ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ም/ል ፕሬዝዳንትና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ “ወደ ፓሪስ የሄድነው የተቀመጠ ሜዳሊያ ለማምጣት ሳይሆን በውድድር አሸንፈን ለማግኘት ነው” ስትል ተናግራለች።
” ውጤት ለማምጣት የተቻላችሁን አድርጋቾኋል ነገር ግን ያሰብነው አልመጣም በፓሪስ ኦሎምፒክ ውጤት ለማምጣት በየፊናችን የምንችለውን አድርገናል ነገር ግን አልተሳካም ነገም ሌላ ቀን ነው ውጤቱ ይመጣል እናንተን አደራ የምለው ስነልቡናችሁን ጠብቁ ዋናው እሱ ነው ውጤቱ በቀጣይ ይመጣል ” ስትል ረዳት ኮሚሽነሯ ተናግራለች።
“ጀግኖች አትሌቶቻችን ለሀገራቸው ባመጡት ድል ባንዲራዋን ከፍ አድርገዋል ከአፍሪካም በውጤቷ የተሻለ ሀገር አድርገዋታል.. ለነሱ ክብር ሁሉ ይገባቸዋል ” ያለችው ምክትል ፕሬዝዳንቷ ” የፓሪስ ኦሎምፒክ አልፏል በውድድሩ ያሸነፋችሁ እንኳን ደስ አሊችሁ ያልተሳካላችሁ ደግሞ ነገም ጊዜ አላችሁ አይዟችሁ” ስትል አበረታታለች።