*…. 19ኙም የክለብ አሰልጣኞች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል……
የመቻል ስፖርት ክለብ ” 83ኛውን ክብረ በዓል ሲያከብር ካቀዳቸው አንዱ የሆነው የግብ ጠባቂዎች ስልጠና በመጪው እሁድ በድሬዳዋ ከተማ መሰጠት የሚጀመር መሆኑ ታውቋል።
ስልጠናውን የሚሰጡት ዓለምአቀፍ ግብ ጠባቂ አሰልጣኞቹ ካሜሮን ኢዩስቶን እና አሌክስ ሄሬዲያ ኢትዮጵያ ሲገቡ በክለቡ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የመቻል ስፖርት ክለብ ቴክኒካል ዳይሬክተር እና የካፍ ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ የስፖርት ክለቡ አሰልጣኞችን አለምአቀፍ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች ማሰልጠን ክለቡ በያዘው መቻል ለኢትዮጵያ ንቅናቄ ለማሳካት ያቀደው ነው ብለዋል።
የካፍ ኢንስትረራክተር አብርሀም መብራቱ ስልጠናው በኢትዮጵያ የሚገኙ የብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ አሰልጣኞች ፣የብሄራዊ ሊግ አሰልጣኞች እንዲሁም የቀድሞ ግብ ጠባቂዎች እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኞች የሚሳተፋበት መሆኑን ጠቁመው ስልጠናው በኢትዮጵያ ያለውን የግብ ጠባቂዎች ስልጠና አንድ እርምጃ ያራምዳል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
- ማሰታውቂያ -
የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ አባል አቶ አሊ ሁሴን ስልጠናው ክለቡ ከሌሎች የስፖርት ክለቦች ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው ለክለቡ ውጤታማነትም የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ኢንተርናሽናል የግብ ጠባቂ አሰልጣኞች ካሜሮን ኢዩስቶን እና አሌክስ ሄሬዲያ በበኩላቸው ስልጠናውን ለመስጠት ኢትዮጵያ በመምጣታቸው ትልቅ ክብር እንደተሰማቸው ገልጸው ስልጠናው ልምድ እና እውቀታቸውን የሚያካፍሉበት እና ለስፖርቱ እድገት የራሳቸውን አሻራ የሚያሳርፋበት ይሆናል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
ምንጭ… ከክለቡ የተገኘ…..