*….የፓሪስ ኦሎምፒክ ባለድሎች ዛሬ በማሪዮት ሆቴል ዕውቅናና ሽልማት ይበረከትላቸዋል….
የኢ .ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሰኔ 4/2016 የተካሄደው የኢትዮጵያ ኦልምፒክ ኮሚቴ ምርጫ በመታገዱ የእግዱን ተግባራዊነት እንዲያስፈጽም በፍርድ ቤት ታዘዘ።
ፍ/ቤቱ በተከፈተው በክረምት ችሎቱ ቢሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የእሎምፒክ ኮሚቴው አካውንት ለሰራተኛ ደመወዝና የሚከፈል ካልሆነ በስተቀር ተለዋጭ ደብዳቤ እስኪደርሳቸው ድረስ ባንኮቹ አካውንቱ ውስጥ ያለው ገንዘብ ባለበት እንዲያቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ሁለት ፌዴሬሽኖችና ሁለት ታላላቅ አትሌቶችን የወኩሉ ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ይግባኝ የኢትዮጵያን ህዝብ አንጡራ ሀብት / ገንዘብ / በሽልማት ሰበብ በህዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ለማድረስ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በቃለ መሃላ መረጋገጡን ተከትሎ የእግድ ትጽ ትዕዛዙን እንደሰጠ አስታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
ችሎቱ ከዚህ በተጨማሪ ግንቦት 5/2017 የተካሄደው የኦሎሜፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤን በተመለከተ የኦሎምፒክ ኮሚቴው መልስ እንዲሰጥ ለመሴከረም 20/2017 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የባህልና ሴፖርት ሚኒስቴር የችሎቱን ተዕዛዝ ለማስፈጸም የት ድረስ ይጓዛል የሚለው አጓጊ ሆኗል። የኮሚቴውም ምላሽ እየተጠበቀ ነው
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክክ ኮሚቴ በአሁኑ ሰአት በማሪዮት ሆቴል ለፓሪስ ኦሎምፒክ ጀግኖች ነእውቅናና የሽልማት መርሃግብር ማከናወን ጀምሯል።