*….. ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 18 ሚሊዮን ብር የመጨረሻው ሀምበሪቾ 8 ሚሊዮን ብር ይደርሳቸዋል….
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የማጠቃላያ መርሃግብር ዛሬ በድሬዳዋ እንደሚካሄድ አክሲዮን ማህበሩ ይፋ አድርጓል።
የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ እንደተናገሩት መርሃግብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ በድሬዳዋ የሚካሄደው የከተማ አስተዳደሩ ለስታዲየም ግንባታ የሰጠውን ትኩረት ለማበረታታትና እውቅና ለመስጠት ታስቦም እንደሆነ ገልጸዋል።
- ማሰታውቂያ -
10 ሚሊዮን ብር የሊጉን ውድድር ላስተናገዱት አዳማ ሀዋሳና ድሬዳዋ ከተሞች እንደሚከፋፈልና አጠቃላይ ለ16 ክለቦች ወደ 195 ሚሊዮን 533 ሺህ 491 ብር ከ85 ሳንቲም ለማከፋፈል መዘጋጀታቸውን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
ለአሸናፊው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደረጃው ወደ 9.7 ሚሊዮን ብር ሲያገኝ ለ16ኛው ሀምበሪቾ ዱራሜ 155 ሺህ ብር እንደሚከፈል አብራርተዋል። እንደ አጠቃላይ ግን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 18 ሚሊዮን 372 ሺህ 928 በር ከ62 ሳንቲም ሁለተኛ ለወጣው ..
መቻል አንድ ሚሊዮን ብር ቀንሶ 17 ሚሊዮን 372 ሺህ 928 ብር ከ62 ሚሊዮን ሲሰጥ ለ16ኛው ሀምበሪቾ ዱራሜ 8 ሚሊዮን ብር እንደሚከፋፈል አስታውቀዋል
የቴሌቭዥን ምስል መብትን በክፍፍሉ ሁሉም ክለቦች እኩል የሚያገኙ መሆናቸው ታውቋል።
19 ክለቦች የሚፋለሙበትና አምስት ክለቦች የሚወርዱበት የ2017 የሊጉ መርሃግብር በዚህ ሳምንት በይፋ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።