” ሚዲያውም በአብዛኛው አሰልጣኞችን እንጂ ተጨዋችችን አይተችም”
ገብረ መድህን ሃይሌ
/ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ/
“ብሄራዊ ቡድኑንም ሆነ ክለብ ማሰልጠን ሰልችቶኛል” ሲሉ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ ተናገሩ።
አሰልጣኙ ዛሬ ከቀትር በፊት በሰጡት መግለጫ ከታንዛኒያና ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ባለው ጨዋታ 4 ነጥብ ለማግኘት አስበን ያሳካነው አንድ ነጥብ ብቻ ነው በተለይ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተሸነፍነው መጥፎ ሆነን ሳይሆን በአጨራረስ ስህተት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
” ከታንዛኒያ ጋር ያገኘነው አንድ ነጥብ አያስከፋም
ዲሞክራቲክ ኮንጎዎች ግን ልምዳቸውን አቅማቸውን ተጠቅመው በሁለት ግብ አሸንፈውናል አስቀድመን ያገኘየውን ዕድል አለመጠቀማችን ዋጋ አስከፍሎናል” ያሉት አሰልጣኙ በአለም ደረጃ ያለንን ልዩነት ታሳቢ አድርጉ ዲ.ኮንጎ በ83 ደረጃ ታንዛኒያ በ30 ደረጃ ይበልጡናል ይህን ታሳቢ ማድረግ አለብን በርግጥ ከወዳጅነት ጨዋታ ውጪ ጂቡቲ ላይ ካስቆጠርየው አንድ ግብ ሌላ አላስቆጠርንም ይሄ ከባድ ነው ችግሩን ለመቅረፍ በረጄም ጊዘዜ እቅድ መስራት ይጠቅብናል በሊጉ ኮከብ ሆነው እየጨረሱ ያሉት የሌሎች ዜጎች ተጨዋቾች ናቸው ይሄም ያለውን ችግር ያሳያል በሊጋችን እውነተኛ 9 ቁጥር የለንም” ሲሉ ተናግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
በነጥብ ጨዋታ 6 ግጥሚያ ያደረጉት አሰልጣኙ 4 ዓለም ዋንጫ 2 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አድርገው 1 ግብ ብቻ ያስቆጠሩት አሰልጣኝ ገብረ መድህን ቶፕ የተባሉትን ተጨዋቾች መርጠን አንድ ግብ ማስቆጠር አልቻሉም ሚዲያውም ተጨዋቾችን አይወቅስም መውቀስ የሚያበዛውም አሰልጣኞችን ብቻ ነው” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
አሰልጣኙ ” ለብሄራዊ ቡድንም ሆነ ለክለብ መስራት ሰልችቶኛል በአሁኑ ወቅት ያሉት ተጨዋቾችም ጥሩ ናቸው ማለት አይቻልም ሁለቱንም በመስራቴቴ ያተረፍኩት ድካም ብቻ ነው” ” በማለት ኮንትራታቸው
ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜ የቀራቸው አሰልጣኝ ገብረ መድህን ገልጸዋል።
አጥቂ ከመፍጠር አንጻር እርስዎስ ምን ሰሩ የተባሉት አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ አጥቂ አይፈጠርም ያለውን አጥቂ አይቼ ውጤታማ ለማድረግ እጥራለሁ እንጂ …እንደ ክለብ ስሰራ ብዙዎች ኮከብ የጨረሱትን አጥቂዎች አበርክቻለሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግን አጥቂ መፍጠር እንዴት ይቻላል ..? ሲሉ ጠይቀዋል።
ከወራት በኋላ ከጊኒ ጋር ስላለው ጨዋታ የተጠየቁት አሰልጣኙ ” ጊኒ ጠንካራ ቡድን መሆኑን እናውቃለን ነገር ግን ለማሸነፍና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ከሜዳ ውጪ የሚደረግ ጨዋታ በሜዳችን ቢሆን የምናወጣውን ውጤት ማሰብ ግን ያስፈልጋል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።