በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ተኛ ሳምንት ጨዋታ ሶዶ ላይ የተገናኙት ወላይታ ድቻና ድሬዳዋ ከተማ ጫዎታቸውን 1 ለ 1 አጠናቀዋል፡፡
በርካታ ተመልካቾች በስቴዲየም የታደሙበት የሁለቱ ክለቦች ጫወታ እጅግ ድንቅ ፉክክርን አስተናግዶ በመጨረሻም ነጥብ አጋርቶ ተጠናቋል፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ ድሬዳዎች ከተማዎች በሁለተኛው ደቂቃ ላይ ከመሀል ሜዳው ጨረር ከ70 ሜትር ርቀት ላይ ሀይቲያዊው የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች ኦልሪሽ ሳውሬይ የማኑኤል ፌይቦን መዘነጋት ተጠቅም ወደ ግብ የመታት ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ተዋህዳ ድሬዎች መሪ መሆን ሲችሉ ከጎልዋ መቆጠር በኃላ ወላይታ ድቻዎች በተደጋጋሚ ጫና ሲፈጥር የነበረው ቶጎዊው አጥቂ ጃኮ አራፋት በ43 ተኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ 1 ለ 1 ተጠናቋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለቱም ክለቦች ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥረው ቢጫወቱም ተጨማሪ ግብ ማግባት ሳይችሉ ቀርተዋል:: በመጨረሻው ደቂቃ ገደማ መጠነኛ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት በወላይታ ድቻ ደጋፊዎች መካከልተነስቶም እንደ ነበር ተገልፆል፡፡ ወላይታ ድቻ በሜዳው ማሸነፍ አልቻለም በአንፃሩ ድሬዎች ከሜዳቸው ውጭ አንድ ነጥብ ይዘው መመለስ ችለዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
የድሬደዋ ከተማ አሰልጣኝ- ዘላለም ሽፈራው
“ከሜዳቸው ውጪ እንደመጫወታቸው ያገኙት ነጥብ የሚያስከፋ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡”
የወላይታ ድቻ ጠንካራ ቡድን መሆኑን ስለምናውቅ አጋጣሚውን ለመጠቀምና ተከላክለን በጥንቃቄ ለመጫወት አቅደን ነበር ፤ተሳክቶልናል”
የወላይታ ድቻ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ
“ተጋጣሚያችንን በማስጨነቅ ተጭነን ለመጫወት ብንሞክርም አጋጣሚዎችን ወደጎልነት መቀየር ባለመቻላችን አቻ ሊንሆን ችለናል “
አስተያየት ይስጡ