መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ5ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።
ሪፖርትቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮ-ኤሌክትሪክ

ሪፖርት | በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ5ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።

አጋራ
አጋራ

ዛሬ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ለፈረሰኞቹ ጎሎቹን ምንተስኖት አዳነ፣ አብዱልከሪም ኒኪማ እና አዳነ ግርማ ማስቆጠር ችለዋል።
አንድ ጊዜ ሞቅ አንድ ጊዜ ቀዝቀዝ ብሎ የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመጀመሪያውን ሙከራ ለማግኘት ብዙ ደቂቃ አልፈጀበትም። 3ኛው ደቂቃ ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በጥሩ ቅብብል ይዘው የገቡትን ኳስ የመስመር አጥቂው ካሉሻ አልሀሰን አክርሮ የመታው ኳስ በግቡ አናት ላይ ወጥቷል። 11ኛው ደቂቃ ላይ የቅ/ጊዮርጊሱ አሜ መሃመድ ተከላካዮችን አታሎ አክርሮ የመታውን ኳስ የኢትዮ-ኤሌክትሪኩ ግብ ጠባቂ ዮሀንስ በዛብህ አውጥቶታል።
ከዚህም በኋላ ቅ/ጊዮርጊሶች በራሳቸው የሜዳ ክፍል በተደጋጋሚ የሚሰሯቸውን ስህተት ተጠቅመው የግብ ዕድል መፍጠር ቢችሉም ወደ ግብነት መቀየር አልቻሉም። 23ኛው ደቂቃ ላይ ኢብራሂም ፎፋና ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ምንተስኖት አዳነ በግንባር በመግጨት ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር።
ከግቡ መቆጠር በኋላ ቅ/ጊዮርጊሶች የተሻለ ብልጫ መውሰድ ቢችሉም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። 34ኛው ደቂቃ ላይ ጋዲሳ መብራቴ ከመስመር እያታለለ ገብቶ አክርሮ የመታው ግሩም ኳስ የግቡን ቋሚ ለትሞ ተመልሷል። 37ኛው ደቂቃ ላይ የኤሌክትሪኩ ዲዲዬ ሊብራ አክርሮ የመታው ኳስ በግብ ጠባቂው ሮበርት ኦዶንካራ ተመልሷል።
የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 5ደቂቃዎች ሲቀሩት(40ኛው ደቂቃ ላይ) የኢትዮ ኤሌክትሪኩ ካሉሻ አልሀሰን የአቻነቷን ግብ አስቆጥሮ ሁለቱን ቡድኖች በአቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት እንዲገቡ ማድረግ ችሏል።
በሁለተኛው አጋማሽ ከተጋጣሚያቸው ተሽለው የተገኙት ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች 51ኛው ደቂቃ ላይ ከመስመር የተሻገረን ኳስ ሄኖክ ካሳሁን በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮት ኳሱ በግቡ አናት ላይ ወደ ውጪ ወጥቷል። 57ኛው ደቂቃ ላይ አሜ መሃመድ ከኢብራሂም ፎፋና የተሻገረለትን ኳስ በግንባር ቢገጨውም ኳሱ ኢላማውን ሳይጠብቅ በግቡ አናት ላይ ወጥቷል።
ከዚህ ሙከራ 4ደቂቃዎች በኋላ 61ኛው ደቂቃ ላይ የቅ/ጊዮርጊሱ አብዱልከሪም ኒኪማ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጪ ያገኘውን ኳስ ተከላካዮችን አታሎ መሬት ለመሬት አክርሮ በመምታት ባስቆጠረው ጎል ቡድኑን በድጋሚ ወደ መሪነት መመለስ ችሏል።
ከግቡ መቆጠር በኋላ ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች ተጭነው ለመጫወት ቢሞክሩም ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ግብ ክልል መድረስ ተስኗቸው ተስተውለዋል። 71ኛው ደቂቃ ላይ የቅ/ጊዮርጊሱ አብዱልከሪም መሃመድ በአስገራሚ ሁኔታ ይዞት የገባውን ኳስ በቀጥታ መትቶት የኢትዮ-ኤሌክትሪኩ ግብ ጠባቂ ዮሀንስ በዛብህ ሲመልሰው ከ6 ወራት ቅጣት በኋላ የተመለሰው የፈረሰኞቹ የፊት መስመር ተሰላፊ አዳነ ግርማ በቀጥታ በመምታት 3ኛውን ጎል ማስቆጠር ችሏል።
75ኛው ደቂቃ ላይ የኤሌክትሪኩ ቢንያም አሰፋ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ በሮበርት ኦዶንካራ ተመልሷል። ከዚህ ሙከራም በኋላ ይሄ ነው የሚባል ሙከራ ሳይደረግ ጨዋታው በቅ/ጊዮርጊስ 3-1 አሸናፊነት ተደምድሟል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮ-ኤሌክትሪክኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን አሸናፈ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮ...

ሸገር ከተማኢትዮ-ኤሌክትሪክዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን 1–0 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አስመዝግቧል።

በአቤኔዘር አበበ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አሳካ በሲቢኢ ኢትዮጵያ...

ቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ተጠባቂዉ የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጲያ ቡና 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በአቤኔዘር አበበ ተጠባቂው 53ኛው የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና 2–1 አሸናፊነት ተጠናቋል።...