መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን EXCLUSIVE | በደደቢት እና በተጫዋቾች መካከል የተነሳው ውዝግብ ክለቡ እና ተጨዋቾቹ ምን ይላሉ፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንደደቢት

EXCLUSIVE | በደደቢት እና በተጫዋቾች መካከል የተነሳው ውዝግብ ክለቡ እና ተጨዋቾቹ ምን ይላሉ፡፡

አጋራ
አጋራ

​ደደቢት ባገዳቸው ሶስት ተጨዋቾች  ማለትም በሳምሶን  ጥላሁን ፤ ዳዊትፍቃዱ እና አክሊሉ አየነው ላይ ለፌዴሬሽኑ ይግባኝ አስገባ:: ተጨዋቾቹ በበኩላቸው ለክለቡ ያስገባነው የይቅርታ ደብዳቤ ከአንድ ወር በላይ ስለቆየ ወደ ፌዴሬሽኑ ሄደን ያቀረብነው ጥያቄ ፍትሀዊ  ምላሽ በማግኘቱ  ደስተኞች  ነን ሲሉ  ለሀትሪክ ስፖርት  ድረ ገፅ ገልፀዋል ::

አቶ ተስፋዬ የደደቢት የሴቶች እግር ኳስ ክለብ የቡድን መሪ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረገፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል

አቶ ተስፋዬ ፡-ተጫዋቾች የገንዘብ ጥያቄ ጠይቀዋል በጥያቄያቸው መሠረት ሂሳባቸው ሲሰራ እንዳውም እላፊ ገንዘብ መውሰዳቸውን አረጋግጠናል፡፡
ተጫዋቾች ቀድመው ከደሞዛችን እሚቆረጥ ግማሽ ክፍያ እያሉ እንደሚወስዱ በኛም በብዙ ክለቦች ይታወቃል ፡፡ይህንንም ለፌዴሬሽኑ በደብዳቤ አስገብተናል፡፡
ልጆቹም ይህንን አውቀው ለክለቡ ይቅርታ ጠይቀዋል ክለቡ ይቅርታቸውን የመቀበልም ያለመቀበልም መብት አለው፡፡ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ከማሳለፉ በፊት እኛን ለማስማማት ምንም አይነት ስራ አልሰራም ይባስ ብሉ ህጉን ሽሯል፡፡ደደቢት የይግባኝ ደብዳቤ ለማስገባት የ3ቀን የግዜ ገደቡን ፌዴሬሽኑ ሳያከብርልን ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡

የይግባኝ ደብዳቤያችንን ለፌዴሬሽኑ እና ለሚዲያው እንዲበተን አድርገናል ሲሉ አቶ ተስፋዬ የደደቢት ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ገልፀዋል፡፡

———————————-
ለደደቢት አግር ኳስ ክለብ የይቅርታ ደብዳቤ ካስገቡተ መካከል ሳምሶን ጥላሁንን በበኩል ከደደቢት የቀረበባቸውን ክስ በተመለከተ ለድህረገፃችን እሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ሳምሶን ጥላሁን:-ለክለቡ የይቅርታ ደብዳቤ አስገብተናል፡፡ሆኖም  ክለቡ ይቅርታችንን ሳይቀበለን ከወር በላይ ቆይተናል ፡፡ ለዛም ነው መፍትሄ ለማግኘት ወደ ፈዴሬሽኑ የሄድነው፡፡ሆኖም  ለክለቡ የመለቀቂያ  ይሰጠን ብለን ስንጠይቅ በሁለት ቀን ውስጥ በድጋሚ ይቀጡ ብለው ነው ደብዳቤ የፃፉብን፡፡
የይቅርታውን ምላሽ ለመስጠት እና የመልቀቂያ ወረቀት ይሰጠን ብለን የጠየቅንበት የደደቢቶች የገዜ ምላሽ አይገናኝም፡፡እንደሚታወቀው ክለቦች የዝውውር እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዝውውር መስኮቱ ሊዘጋብኝ ስለሆነ ይህን እርምጃ ወስደናል፡፡

ፌዴሬሽኑም በሰጠን ፍትሀዊ የሆነ ምላሽ ደስተኞች ነን ሲል ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ገልጿል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የሚዲያ ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ

ለፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ ስልጠና ተሰጠ የኢትዮጵያ እግር...

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየዝውውር ዜናዎች

እዮብ አለማየሁ ለወልዋሎ እንዲጫወት ተወሰነ

እዮብ አለማየሁ ጉዳይ  ውሳኔ አገኘ። ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱ ተጫዋቾች ለመቻል እንዲጫወቱ ሲወሰን ቅጣትም ተጣለባቸው

አለምብርሀን ይግዛው እና አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ጉዳይ ውሳኔ አገኘ። በያዝነው የክረምቱ የዝውውር...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፌደሬሽኑን ለ3ኛ ጊዜ ለመምራት ብቸኛ እጩ ሆነው ቀርበዋል።

እጩ ሆኜ መቅረቤን እንጂ ሌሎች ተፎካካሪዎች ለምን በፕሬዝደንትንት ለመወዳደር እንዳልቀረቡ የማውቀው ነገር...