የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
- አሸናፊ ፊዳ (አርባምንጭ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- ባህርዳር ከተማ-አርባምንጭ ከተማ
- መቐለ 70 እንደርታ-አርባምንጭ ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ-ሲዳማ ቡና
- አርባምንጭ ከተማ-ምድረ ገነት ሽረ
- አርባምንጭ ከተማ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ዳዊት ታደሰ (ሃዋሳ ከተማ) : የመታወቂያ ቁጥር EFF-18-067 ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ሃዋሳ ከተማ ፋሲል ከነማ
- ሃዋሳ ከተማ-መቻል
- ሃዋሳ ከተማ-ነገሌ አርሲ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ-ሃዋሳ ከተማ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ -ሃዋሳ ከተማ
- ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ተስፋዬ በቀለ (ነገሌ አርሲ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- ሀዲያ ሆሳዕና-ነገሌ አርሲ
- ነገሌ አርሲ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ወላይታ ድቻ-ነገሌ አርሲ
- ነገሌ አርሲ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ቡልቻ ሹራ (ሸገር ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ።
- ሸገር ከተማ-ሃዋሳ ከተማ
- ሸገር ከተማ-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ሸገር ከተማ-ሲዳማ ቡና
- ፋሲል ከነማ-ሽገር ከተማ
- ሸገር ከተማ-መቻል
- ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ሱራፌል ዳኛቸው (ሲዳማ ቡና) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ
ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ሲዳማ ቡና-መቻል
- ሲዳማ ቡና-ኢትዮጵያ መድን
- ሽገር ከተማ-ሲዳማ ቡና
- ባህርዳር ከተማ-ሲዳማ ቡና
- ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ነገሌ አርሲ : ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ37ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የነገሌ አርሲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- አለኝታ ማርቆስ
- ገብረመስቀል ዱባለ
- ዴሲሬ ፓስካል
- ተስፋዬ በቀለ
- ፍቅሩ ጴጥሮስ
- ኪቲካ ጅማ
- በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ37ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የማስታወቂያ የኦቤኤን ባክግራውንድ ቢልቦርድ መስታወትን ስለመሰባበራቸው ሪፖርት ተደርጓል። ስለሆነም ክለቡ የተሰበረውን የማስታወቂያ ቢልቦርድ እንዲያሰራ ወይም ድርጅቱ አሰርቶ የሚያቀርበውን ዋጋ እንዲከፍል ወስኗል።
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ37ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በግራ ጥላፎቅ የነበሩ የክለቡ ደጋፊዎች ወደ ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ቁሳቁሶችን ስለመወርወራቸው ጨዋታው ከተጠናቀቀም በኋላ በስታድየሙ አካባቢ ከተጋጣሚ ቡድን ጋር ድንጋይ በመወራወር ከፍተኛ ሁከትና ችግር ስለመፍጠራቸው፣በውርወራውም ወቅት በአንዳንድ ደጋፊዎች ላይ ጉዳት | ስለመድረሱ እንዲሁም የፖሊስ ሀይል በወሰደው : ተመጣጣኝ እርምጃ (ጥይት ወድሰማይ በመተኮስ) ችግሩ ስለመብረዱ ሪፖርት ተደርጓል። ስለሆነም በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 3 ሀ እና ለ መሠረት የክለቡ ደጋፊዎች ላጠፋት ጥፋት ክለቡ ብር 50 000 /ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል እንዲሁም ክለቡ በሚያደርገው ቀጣይ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች ወደ ስታድየም ገብተው እንዳይመለከቱ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ፋሲል ከነማ ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ37ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በቀኝ ጥላፎቅ የነበሩ የክለቡ ደጋፊዎች ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቁሳቁሶችን ስለመወርወራቸው ጨዋታው ከተጠናቀቀም በኋላ በስታድየሙ አካባቢ ከተጋጣሚ ቡድን ጋር ድንጋይ በመወራወር ከፍተኛ ሁከትና ችግር ስለመፍጠራቸው ፣በውርወራውም ወቅት በአንዳንድ ደጋፊዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ እንዲሁም የፖሊስ ሀይል በወሰደው ተመጣጣኝ እርምጃ (ጥይት ወድሰማይ በመተኮስ) ችግሩ ስለመብረዱ ሪፖርት ተደርጓል። ስለሆነም በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 3 ሀ እና ለ መሠረት የክለቡ ደጋፊዎች ላጠፋት ጥፋት ክለቡ ብር 50 000 /ሃምሳ ሺህ/እንዲከፍል እንዲሁም ክለቡ በሚያደርገው ቀጣይ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች ወደ ስታድየም ገብተው እንዳይመለከቱ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
አስተያየት ይስጡ