ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ብጥብጥ ፈጥረዋል በሚል የገንዘብ እና የመጨረሻ ጨዋታቸውን በዝግ እንዲያደርጉ ተወሰነ።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሀግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍፁም ጥላሁን ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ፋሲል ከነማን 1ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል።
በጨዋታው ላይ የማስታወቂያ የኦቢኤን ባጎራውንድ ቢል ቦርድ እንዲያሰሩ ወይም ድርጅቱ አስልቶ በሚያወጣው ዋጋ ማሰራት እንዳለባቸው ሲወሰን የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በሜዳው የግራ ጥላ ፎቅ እንዲሁም የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በቀኝ ጥላ ፎቅ አካባቢ ቁሳቁሶችን በመወርወር ጨዋታው ከተጠናቀቀም በኋላ ሁለቱም ክለቦች ድንጋይ በመወራወራቸው ከፍተኛ ሁከት እና ብጥብጥን በስታዲየሙ ዙሪያ በመፍጠራቸው በአንዳንድ ደጋፊዎች ላይ ደግሞ ጉዳት በመድረሱ ከዚህ የበለጠ የከፋ ጉዳትም እንዳይደርስ ፓሊስ ተመጣጣኝ ዕርምጃን ወስዶ (ጥይት ወደ ላይ በመተኮስ) ችግሩ እንዲበርድ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ አክሲዮን ማህበሩ ክለቦቹ ለፈፀሙት ጥፋት በተመሳሳይ እያንዳንዳቸውን የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እና የመጨረሻውን የሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ከወልዋሎ ጋር የሚከውኑትን መርሀግብር ያለ ተመልካች በዝግ እንዲያደርጉ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
አስተያየት ይስጡ