መነሻ ገጽ Uncategorized የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድንን በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሩብ ፍጻሜ ለማድረስ እንደሚሰሩ አዲሱ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተናገሩ።  
Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድንን በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሩብ ፍጻሜ ለማድረስ እንደሚሰሩ አዲሱ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተናገሩ።  

አጋራ
አጋራ

 

አዲሱ አሰልጣኝ ዋልያዎቹን ለአፍሪካ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ለማድረስ ይሰራሉ አሰልጣኙ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በ100 ሺህ ብር ወርኃዊ ደመወዝ ዋልያዎቹን ለማሰልጠን የሁለት ዓመት ኮንትራት ተሰጥቷቸዋል።

ኮንትራቱ ከመጋቢት 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ ነው።

በሁለት ዓመት ቆይታቸው ዋልያዎቹን ካሜሮን ለምታስተናግደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድኑን ለማሰልጠን የተወዳደርኩት የተሻለ ነገር ለመስራት ስለሆነ ለአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ ብቻ ሳይሆን ለሩብ ፍጻሜ ለማድረስ እሰራለሁ ብለዋል።

የገቡት ውል ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫና ለቻን ውድድር ማሳለፍን እንደሚያካትትም ገልጸዋል።

“ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ብቻ አይደለም ለቻን ውድድር ማሳለፍ ካልቻልኩ ሁለት ዓመት አልጠብቅም፤ በራሴ ፍቃድ እለቃለሁ” ብለዋል።

“በአፍሪካ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ ማድረስ ትግል እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን በኅብረት ከሰራን የፈለግንበት መድረስ እንችላለን” ሲሉም አክለዋል።

ዋልያዎቹን ለማሰልጠን የተወዳደሩት ገንዘብ ፈልገው ሳይሆን በእግር ኳሱ አሻራቸውን ለማስቀመጥ መሆኑን ተናግረዋል አሰልጣኙ።

ከቀድሞ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች፣ የስፖርት ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች ጋር እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

“ተባብረን ከሰራን ብዙ እርምጃ እንጓዛለን፤ ስለሆነም ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን፤ እኔም ከሁሉም አካላት ጋር ተባብሬ ለመስራት ፍቃደኛ ነኝ” ብለዋል።

የተሻለ ልምድና ወቅታዊ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች በቡድኑ እንደሚያካትቱ የገለጹት አሰልጣኝ አሸናፊ በመጪው ግንቦት ሶስት የወዳጅነት ጨዋታዎችን የማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል። 

የወዳጅነት ጨዋታዎቹን ከምስራቅ፣ ከደቡብና ከምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር እንደሚያካሂዱም ይፋ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዘርይሁን ቀቀቦ አሰልጣኝ አሸናፊ በላይሰንስ፣ በልምድና በወቅታዊ አቋም መመረጣቸውን ተናግረዋል።

“የአገር ውስጥ አሰልጣኝ ለመቅጠር የተገደድነው ባለፉት ዓመታት ከውጭ አሰልጣኞች የተሻለ ውጤት በማስመዝገባቸው ነው” ብለዋል።

ከውጤት ማጣት እንዲሁም ከገንዘብ ወጪ አንጻር ሲታይ የውጭ አገር አሰልጣኝ ከጥቅሙ ጉዳቱ ማመዘኑን ነው አቶ ዘርይሁን የተናገሩት።

አሰልጣኙ የመኪና፣ የህክምና፣ የሞባይል ካርድና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ጨምሮ በወር 100 ሺህ ብር እየተከፈላቸው ለሁለት ዓመት ብሄራዊ ቡድኑን ይመራሉ።

ቡድኑን ለ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ትልቅ ኃላፊነት እንደተጣለባቸው የገለጹት አቶ ዘርይሁን የሚፈለገውን ውጤት ካላመጡና የቀጣሪውን አካል መልካም ስም የሚያጎድፍ መግለጫ ከሰጡ ውላቸው እንደሚቋረጥ አስታውቀዋል።

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ። የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል።...