መነሻ ገጽ Uncategorized ​አዲስ አበባ ከተማ ሱራፌል ጌታቸውን ወደ ቡድኑ እስከ ነገ ካልመለሰ እገዳ ሊጣልበት ነው
Uncategorized

​አዲስ አበባ ከተማ ሱራፌል ጌታቸውን ወደ ቡድኑ እስከ ነገ ካልመለሰ እገዳ ሊጣልበት ነው

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በተቀላቀለበት የእዚህ ዓመት ላይ በወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በእዚህ ዓመት ከሙገር ባስመጣው እና ለሁለት ዓመት ባስፈረመው የቀድሞው የኢትዮጵያ ታዳጊ የወጣት እና  በአሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የአሰልጣኝነት ዘመንም ለሀገራችን ተመርጦ በነበረው ድንቁ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሱራፌል
ጌታቸው ላይ በቅርቡ የስንብት ውሳኔን አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም ወጣቱ ተጨዋቹ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ባስገባው አቤቱታ እና ምላሽ መሰረት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የዲስፕሊን ኮሚቴ ጉዳዩን በሚገባ ከተመለከተው እና ከመረመረው በኋላ
ውሳኔ ሊሰጥበት ችሏል፤ የተጨዋቹን ስንብትም ህገ-ወጥም ነው ብሎታል፡፡

PicsArt_1490192912225

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በቡድኑ ተጨዋች ሱራፌል ጌታቸው ላይ ስንብትን አስተላልፎ የነበረው ተጨዋቹ በፕሪምየር
ሊግ የጅማሬ ጨዋታዎች ላይ ለክለቡ ከ15 ጨዋታዎች ውስጥ በአንዱም መጫወት አልቻለም፤ ከጉዳቱ በአስቸኳይ አገግሞም
በመምጣት ክለቡን አልጠቀመም፤ ብቃቱንም ማሻሻል አልቻለም፤ ወደ ቡድኑ እንዲቀላቀልም ደብዳቤ ቢፃፍለትም በማናለብኝነት የክለቡን የዲሲፒሊን ደንብ እና በኢትዮጵያ እግር
ኳስ ፌዴሬሽን ፊት የገባኸውን ውል በተለይም የክለቡን እና የፌዴሬሽኑን ደንብ ማክበር የሚለውን በመጣስ የክለቡን ህጋዊ ደብዳቤ አልቀበልም ብሎ የክለቡን ውሳኔ የማደሪያ ካምፕ ውስጥ እስኪለጠፍ ደረጃ አድርሶታል ከእዚያ ውጪም በጉዳቱ ወቅት የተሰጠውን የእክምናውን የእረፍት ወቅት ጨርሶ ወደ ልምምድ መግባት ሲገባው ባለመግባቱ እና ክለቡ እጅግ በወረደ አቋም ላይም እየተገኘ ባለበት ሰዓት ክለቡን ለማዳን ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ሲገባው ለቢሮ ሳያሳውቅ ከ11 ቀን
በላይ መጥፋቱ በሚሉ ውሳኔዎች ክለቡ ተጨዋቹን ሊያሰናብት ቢችልም ተጨዋች ሱራፌል ጌታቸውም ለእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ባስገባው አቤቱታ ከክለቡ የተሰናበትኩበት መንገድ ፈፅሞ ተገቢ አይደለም የክለቡ ልምምድ ላይ ሆኜ በደረሰብኝ ጉዳት ምክንያት እረፍት ላይ ባለሁበት ሰዓት ነው የአቋም መውረድ ይታይብሃል በማለት ከውል ውጪ ከክለቡ እንድሰናበት የተደረግኩት ጉዳዬም ይታይልኝ በሚል ባቀረበው የአቤቱታ መልስ ጉዳዩን የዲስፕሊን ኮሚቴው በጥልቀት እና በዝርዝር ከመረመረው
በኋላ ውሳኔ ሊሰጥበት ችሏል፡፡

PicsArt_1485956162325

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴም የሁለቱን አካላቶች ጉዳይ ሐሙስ ዕለት ከተመለከተም በኋላ ስንብቱን ህገ-ወጥ በማለት ውሳኔውን ይፋ ሊያደርግ ችሏል፤ የኢትዮጵያ
እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተጨዋች ሱራፌል ጌታቸው ለክለቡ ግልጋሎት መስጠት ያልቻለው በልምምድ ሜዳ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት መሆኑን ክለቡ ያልካደው እውነት ሆኖ ሳለ የአቅም መውረድ ይታይብሃል በማለት ማስጠንቀቂያ መስጠት
ተገቢ ከመሆኑም በላይ ከክለቡ የዲስፕሊን ደንብ አንፃር ሲመዘን በስፖርት ባለሙያዎች እና ስፖርተኞች ሊፈፀሙ የሚችሉ የስነ-ምግባር ጉድለቶችና የውሳኔ ደረጃዎች በሚለው አንቀፅ 12 ስር ከተገለፁት ጥፋቶች ውስጥ የአቅም መውረድ
እንደጥፋት አልተጠቀሰም፤ የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ በፃፋቸው ማስጠንቀቂያዎች ላይም ተጨዋቹ የተላለፈው የትኛውን የዲስፕሊን ደንቡን ክፍል እንደሆነ አይገልፅም፤ እንዲሁም ተጨዋቹ በጉዳት ላይ ሆኖና በህክምና ላይ በነበረበት ጊዜ
ብቃቱን እንዲያሻሽል ማስጠንቀቂያ መፃፉና ከክለቡ የተፃፈ ደብዳቤ አልቀበልም ብሏል በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት አግባብነት የደንብም ሆነ የውል መሰረት የሌለው
መሆኑን እና ለተጨዋቹ የተሰጠው የስንብት ደብዳቤ የቅጥር ውሉን የክለቡን የዲስፕሊን ደንብ እንዲሁ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሸሻለው የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ያላደረገ
በመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ መሆኑ ተጠቅሶ የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ ለተጨዋቹ ያልተከፈለውን ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎ የውል ጊዜው እስኪጠናቀቅ ድረስ ወደ ስራው እንዲመለስ ክለቡ ተጨዋቹን ወደ ስራ ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆነ ውዝፍ ደመወዙንና የቀሪውን የውል ጊዜ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እንዲያሰናብተው እና ክለቡ ውሳኔው ከደረሰው ቀን ጀምሮ ውሳኔውን ካልፈፀመ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተሸሻለው
የዲስፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 68 8 መሰረት ፌዴሬሽኑ ከሚመራው ማናቸውም እግር ኳስ ውድድሮች ላይ ክለቡ እንዳይሳተፍ ተወስኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ ተጨዋቹን እስከነገ ወደቡድኑ ካልመለሰ እና አልያም ደግሞ ለተጨዋቹ እንዲፈፅሞ የተወሰነበትን ክፍያ ሊሰጥ ካልቻለ ህገዳው ሊፀናበት እንደሚችልም ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሐሙስ ዕለት ለአዲስ አበባ ከተማው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሱራፌል ጌታቸው ተገቢ እና ፍትሃዊ ውሳኔ መስጠቱን ተከትሎም ተጨዋቹ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ፤ ለዲስፕሊን ኮሚቴው፤ ለአቶ
ጌታቸው አበበ፤ ለአቶ ዳንኤልና ከጎኑ ሆነው ለረዱት ሌሎች አካላቶችም ምስጋናውን ሊያቀርብላቸውም ችሏል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ። የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል።...