ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም ተለያዩ
ላለፉት 4 አመታት በ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቆዩት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም ቀሪ የፊርማ ግዜ እያላቸው ክለቡ ከሀላፊነታቸው አንስቷል ፡፡
ለአስልጣኙ ከሀላፊነታቸው መነሳት በ2009 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ አንደኛ ዙር ያስመዘገቡት ውጤት ቀዳሚ ድርሻውን ይወስዳል፡፡
ክለቡ በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ አንደኛው ዙር በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በ15ኛ ደረጃ ይገኛል፡፡
በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ በዋና አሰልጣኝነት የክለቡ ምክትል አሰልጣኝ ሲሳይ እና ከ20 አመት በታች አሰልጣኝ የሆኑት ግርማ ፀጋዬ እንደሚመሩት ዛሬ የክለቡ ቦርድ ወስኗል፡፡
አስተያየት ይስጡ