መነሻ ገጽ Uncategorized በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቶታል
Uncategorized

በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቶታል

አጋራ
አጋራ

1489349316-picsay

21ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ክለቦች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል እየተሳተፈ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ወደ ወሳኙ የምድብ ድልድል ለመግባት የ90 ደቂቃ እድሜ ብቻ ቀርቶታል፡፡

1489349402-picsayበኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11:30 ሲል የጀመረው የሊዮፓርድ እእና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በ28ኛ ደቂቃ በምንተስኖት አዳነ ጎል አሸንፎ ሊወጣ ችልዋል፡፡በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ በ 80ኛ ደቂቃ ላይ የጨዋታው ጎል አስቆጣሪ ምንተስኖት አዳነን በሁለት ቢጫ ከሜዳ አሰናብተዋል፡፡

በጨዋታው ሂደት የዳኛ ውሳኔ  ላይ ሰፊ የአመራር ችግር እንደነበር ተውቋል፡፡


ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድሩ ቅድመ ማጣሪያ የሲሸልሱን ሻምፒዮን ኮት ዲኦርን በሳላዲን ሰኢድ (3)፣ አስቻለው ታመነ እና በሀይሉ አሰፋ ጎሎች በድምሩ 5ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፎ ወደዚህኛው ዙር ያለፈ ሲሆን ተጋጣሚው ኤሲ ሊዮፓርድስ በበኩሉ የካሜሮኑን ዩ ኤስ ኤም ዴሉምን በሜዳው 1ለ0 አሸንፎ ከሜዳው ውጭ ደግሞ 2ለ1 ተሸንፎ ነገር ግን ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የበቃ ነው፡፡ የሁለቱ ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታ በሳምንት ጊዜ ልዩነት ውስጥ የሚከናወን ሲሆን የሁለቱ ጨዋታዎች የደርሶ መልስ አሸናፊ በውድድሩ ምድብ ድልድል ውስጥ መግባት እና ከሌሎች 3 ክለቦች ጋር በደርሶ መልስ የመጫወት እድልን ከማግኘቱ በተጨማሪ የአምስት መቶ ሀምሳ ሺህ ዶላር ወይም ወደ አስራ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ተሸላሚም ይሆናል፡፡ ተሸናፊው ቡድን በአንፃሩ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ውስጥ ለመግባት ከሌላ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ቡድን ጋር በደርሶ መልስ የመጫወት እድል የሚኖረው ሲሆን ወደ ምድብ ድልድሉ የሚያልፍ ከሆነም የቻምፒዮንስ ሊጉን ያክልም ባይሆን ጠቀም ያለ የገንዘብ ሽልማት አብሮ የሚበረከትለት ይሆናል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ ኤሲ ሊዮፓርድስክለቡ እ.ኤ.አ በ1953 ዓ.ም የተመሰረተ እና ሙሉ ስሙ አትሌቲክ ክለብ ሊዮፓርድስ ሲባል በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዴኒስ ሳሱ ኒጉኤሶ ስም የተሰየመ 5000 ተመልካቾችን ማስተናገድ የሚችል ስታዲየም ባለቤት ነው፡፡ ምንም እንኳን ክለቡ ረዥም የምስረታ እድሜ ቢኖረውም የውጤታማነት ታሪኩ ግን በቅርብ አመታት የተመዘገቡ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይም እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ክለቡ ያለዋንጫ ያጠናቀቀበትን የውድድር ዓመት ማግኘት ከባድ ነው፡፡ በታሪኩ ያስመዘገባቸውን 3 የኮንጎ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊነት፣ 5 የኮንጎ ዋንጫ እና በ2012 ያሳካውን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ድሎች ያገኘው ከላይ ከተጠቀሰው ዓመት ወደዚህ መሆኑን መመልከትም የክለቡን የቅርብ ጊዜያት ተከታታይ ውጤታማነት ማረጋገጫ ነው፡፡ የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ የፊታችን ሳምንት እሁድ መጋቢት 10/2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት እንደሚከናወን ተረጋግጧል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ። የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል።...