ፌደሬሽኑ ባለስድስት ፎቅ ህንፃ ለመግዛት የመጨረሻው ውሳኔ ላይ ደርሷል
የኢትዮጵያን እግር ኳስ በበላይነት
የሚመራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና
አለም አቀፍ እግር ኳስ የበላይ አዛዥ የሆነው
ፊፋ በመጪው ሳምንት በአዲሱ ህንፃ ዙሪያ
የኮንትራት ስምምነት ፊርማ ይፈራረማሉ፡፡
ፊፋ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
አሁን ከሚገኝበት የፌዴሬሽኑ በር ወጥቶ
ደረጃውና የጠበቀ የራሱ ፅ/ቤት እንዲኖረው
በማሰብ ለፌዴሬሽኑ ቢሮ የሚሆን ህንፃ ግዥ
የሚውል 3 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ለመስጠት
መዋሉ ይታወሳል፡፡ ፊፋ ለፌዴሬሽኑ ቢሮ
የህንፃ ግዥ የሚውል 3 ሚሊየን ዶላር
የወይም በወቅቱ ምንዛሬ ከ75-80 ሚልየን
የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመስጠት
ከመወሰን ወጪ እስከ አሁን ገንዘቡ ያልተለቀቀ
ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በመጪው ሳምንት
ከሚያደርጉት የፊርማ ገንዘብ እንደሚለቀቅና
በኋላ ፌዴሬሽኑ የራሱ የሆነ ባለስድስት ፎቅ
ህንፃ ባለቤት እንደሚሆን ነው የመረጃም ነጮች
በተለይ ለሀትሪክ የሚጠቁሙት፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፊፋ የ3
ሚልየን ዶላር ለቢሮ የሚሆን ህንፃ መግዣ
ገንዘብ ከፊፋ እንደሚለቀቀለት ቃል ከተገባ
በኋላ የፌደሬሽኑ ሰዎች የተለያዩና ህንፃዎች
ሲያፈላልጉ የቆዩ ቢሆንም በተለያዩ ወገኖች
አማካይነት ካቀረቡላቸው ህንፃዎች የተሻሉና
የፌዴሬሽኑን ሰዎች ያገኘውና የመጀመሪያ
ምርጫ የሆነው ካፒታል ሆቴል አካባቢ
የሚገኘው ባለስድስት ፎቅ ህንፃ በመሆኑ ይህ
ህንፃ ቀጣዩ የፌዴሬሽኑ ቢቶችና ንብረት ሊሆን
እንደሚችል ነው እየተነገረ ያለዉ፡፡ አዲሱ ቢሮ
ካፒታል ሆቴል የሚገኘው ባለስድስት ፎቅ
መሆኑ አይቀሬ ነው በማለት በተለይ ለሀትሪክ
መረጃውን የሰጡት ምንጮች እነደዚህ
አይነቱ ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸውን ምን
እንደሆነ ሲናገሩ ከህንፃው ግንባታ ከቀረበው
ዋጋ ከቦታው ምቹነትና ማዕከላዊነት አንፃር
ካፒታል ሆቴል አካባቢ የሚገኘው ባለስድስት
ፎቅ ህንፃ ከታዩት ህንፃዎች የተሻለና
የመጀመሪያው ምርጫ በመሆኑ ፌደሬሽኑ
በእነዚህ ምክንያቶች ህንፃውን ለመግዛት
እንዲወስን ነው የሚገልፁት፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በያዝነው
ሳምንት በአንድ ቀን አሊያም በቀጣይ ሳምንት
በሚያደርገው ስብሰባ ትልቁ አጀንዳው የህንፃው
ግዥው ጉዳይ ሲሆን በእለቱ በሚደረገው
ስብሰባም የህንፃ ግዥው ጉዳይ የመጨረሻው
ውሳኔ እንደሚያደገኝና በውሳኔው መሰረት
በሚቀርብረው የውሳኔ ሃሳብና ከፊፋ ጋር ከማድረግ የኮንትራት ስምምነት በኋላ ካፒታል ሆቴል አካባቢ የሚገኘውን ባለስድስት ፎቅ የግል ህንፃ የግል ንብረቱ እንደሚያደርገው ነው ታማኝ የዜና ምንጮች በተለይ ለሀትሪክ የገለፁት፡፡
ከምስረታ እድሜው ጀምሮ በአዲስ
አበባ እግር ከስ ፌደሬሽን ቀመኔውን አድርጎ
የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
በቀድሞው አመራር ኢንተርኮንቲኔንታል
ሆቴል አካባቢ ከሚገኝ ህንፃ ውሰጥ በገዛው
ባለ1 ፎቅ በአሁን ሰአት እየተጠቀመበት
ሲሆን በቀጣዩ ካፒታል ሆቴል አካባቢ
የሚገኘውን ባለስድስት ፎቅ ህንፃ በተያዘው
እቅድ መሰረት ግዥውን ተግባራዊ ካደረገ
በፌዴሬሽኑ በተያዘው እቅድ መሰረት
ግዥውን ተግባራዊ ካደረገ በፌደሬሽኑ
የምስረታ ታሪክ የራሱ ህንፃ ባለቤት ሆና
ይመዘገባል ማለት ነው፡፡ ሁሌም ወደስልጣን
የሚመጡ የፌደሬሽኑ አመራሮች ከፊፋ
በየአመቱ የሚለቀቀውን የ500 ሺህ ዶላር
ድጎማ ብቻ ነው፡፡ የሚጠባበቁት ከዚህ የዘለለ
ለተለያየ ጥረትን ግንኙነት ቢያደርጉ ከህንፃ
በዘለለ የአገሪቱ እግር ኳስ ብዙ ጥቅሞችን
ማግኘት ይችል ነበር፡፡ በማለት በቀጥታ
አስተያየትን የሚሰጡ ወገኖች አሁን በትንሽ
ስጥረት ከተገኘው ትልቅ ጥቅም በመማር
በቀጣይ አገሪቱ ከፊፋና ከካፍ የተለያዩ
ጥቅሞችን በምታገኝበት ዙሪያ በደካሙ
አገራችን ታተርፋለች ሲሉ አስተያየታቸውን
ሰጥቷቸዋል፡፡
አስተያየት ይስጡ