መነሻ ገጽ ሪፖርት ደቡብ ፓሊስ የመጀመሪያ 3 ነጥቡን በሜዳው በሰፊ የጎል ልዩነት ማሳካት ችሏል
ሪፖርትናሽናል ሲሜንትየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግደቡብ ፖሊስ

ደቡብ ፓሊስ የመጀመሪያ 3 ነጥቡን በሜዳው በሰፊ የጎል ልዩነት ማሳካት ችሏል

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 4ኛ ሳምንት በምድብ-ለ  ደቡብ፡ፖሊስ ከ ናሽናል ሲሜንት አገናኝቶ ባለሜዳዎቹ ደቡብ ፓሊሶች  በሰፊ የጎል ብልጫ 6-0 በሆነ ውጤት  ናሽናል ሲሜንትን መረምረም ችልዋል።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ኳስን ተቋጣጥሮ በመጫወት ባለሜዳዎቹ ደቡብ ፖሊሶች ብልጫ ነበራቸው፡፡ በ4ተኛ ደቂቃ  አገኘው ለኪሳ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን ፍ.ቅ.ም እራሱ አገኘው አስቆጥሮ የማህል ዳኛው ሽሮታል።13ተኛ ደቂቃ ከአኘው የተቀቀለውን ኳስ ብሩክ ኤልሊያስ ወደ ግብ ቀይሯታል።በኳስ በቁጥጥር እንግዳዎቹ የተሻሉ ነበሩ። ወደ ግብ ጋር በመድረስ እና ሙከራ በማድረጉ ደቡብ ፓሊስ ጥሩ ነበር።ብሩክ ኤሊያስ,ኤሪክ ሙራንዳ እና አገኘው በተደጋጋ ሙከራ በማድረግ ጫና ፈጥረዋል በ44 በደቂቃ ኤሪክ ሙራንዳ ፍፁም ቅጣት ምት ጎል 2ለ0 እረፍት ወጥተዋል። በሁለተኛው አጋማሽ ደቡብ ፓሊስ በኳስ ቁጥጥሩ ተሻለው ነበር በተለይም ቢኒያም አድማሱ ጥሩ ሲንቀሳቀስ ነበር።

በጫወታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ብሩክ ኤሊያስ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ በ70ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል ወዲያው በመልሶ ማጥቃት ከኤሪክ ሙራንዳ የተሻገረለትን አገኘው ሊኪሳን ቀይቆ የገባው አበባው ዮሐንስ ግብ እስቆጥሮ 4ለ0 አድርጎታል።በ82  በደቂቃ ሙዲን አብደላ እንዲሁም ኤሪክ ሙራንዳን ቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው በሀይሉ ወገኔ በ89ኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሮ 6ለ0 በሆነ ውጤት ጫዋታው ተጠናቋል።
ደቡብ ፖሊስ በ3 ጨዋታ 4 ነጥብ በማግኘት  3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል 

የአሰልጣኞች አስተያየት

 ደቡብ ፓሊስ- አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ

 ያገኘናቸውን እድሎች መጠቀማችን ጨዋታውን ተቆጣጥረን ግቦችን አስችናል።በእራሳችን ክፍተተት ያጣናቸው ነጥቦች ነበሩ አሁን ወደ አሸናፊነት ተመልሰናል በቀጣይ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪእንሆናለን።

 ናሽናል ሴሜንት –  አሰልጣኝ ፍቅሩ ተዘራ

በመጀመርያ አጋማሽ ኳስ ይዞ በመጫወት ጥሩ ነበርን ነገር ግን ግብ በማግባቱ የተሻሉ ነበሩ ምንም ማረግ አልቻልንም ተጫዋቾቹቼ ሜዳው ከብዱቸው ነበር። ባለፉት ጫዋታዎች ጥሩት ነበርን በቀጣይ ወደ አሸናፊነት። እንመለሳለን።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

አሰልጣኝ ጳውሎስ (ማንጎ) ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ተሰናበቱ

አዲስ የተቀጠሩት እና ዛሬ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ቡድኑን በአንድ ጨዋታ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ለሌብነት ምቹ ወደ መሆን የቀረበው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ?

ለወትሮ ሀሜት የማያጣው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ትኩረት ሊሰጠው ወደ ሚገባው ምዕራፍ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ሦስት ስመ ጥር አሰልጣኞች ሦስት ክለቦች ለማትረፍ በሀላፊነት ተረክበዋል

ላለመውረድ እየተጫወቱ የሚገኙ ሦስት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በሦስት የሚታወቁ አሰልጣኞች ይመራሉ። በኢትዮጵያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግጋሞ ጨንቻ

የጋሞ ጨንቻው ወጣቱ አሰልጣኝ ማነው ?

ራሱ የመሠረተውን ክለብ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እያንደረደው የሚገኘው አሰልጣኝ። ከአመት አመት አዳዲስ...