በ6 ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀግብር ቅዳሜ አና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታወች ቀጥሎ ሲውል እሁድ ታህሳስ1 ከሚደረጉ የክልል ጨዋታዎች መካከል አርባምንጭ ላይ አርባምንጭከተማ የሊጉን መሪ አዲስ አዳጊውን ውልዋሎ ዓዲግራት.ዩ ሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይ አንዳንድ ነጥቦች እናያለን፡፡
የመጀመሪያውን 4 ጨዋታወች በውጤት ቀውስ ውስጥ የነበረው አርባምንጭ ከተማ በ5 ሳምንት መርሀግብር መከላከያን በሜዳው በታዳግው አጥቂ ብርሀኑ አዳሙ ና በተከላካዩ ፀጋዬ አበራ ሁለት ግቦች 2-0 በማሸነፍ በጥቂቱ እፎይታን ቢያገኙም የነገውን ጨዋታ በማሸነፍ ሙሉ ለሙሉ ከወራጅ ቀጠናው በመውጣት ወደ ዋንጫው ፉክክር ግስጋሴ ለመቀላቀል እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡
በአንፃሩ ውልዋሎ ከመጀመሪያው ሳምንታት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ቢጀምርም ቡድኑ ያለበትን ክፍተት በማስተካከል በ4 ሳምንት አዲስአበባ ላይ ኢትዮ-ኤሌክትሪክን 3-1 አንዲሁም በ5 ሳምንት ዓዲግራት ላይ ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 በማሸነፉ በ9 ነጥብ የሊጉ መሪ መሆን ችሏል፡፡
የአሰልጣኝ ብርሀኔ ስብስብ ኳስን መሰረት አድርጎ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን የያዘ ብድን ስሆን፡፡ በነገውን ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ኳስን መሠረት ያደረገ የጨዋታ ስልት እደሚተገብሩ ይጠበቃል፡፡
የፀጋዬ ኪዳነማርያሙ አርባምንጭ ከተማ መከላከያ ላይ ይዞት የገባውን የ3-5-2 አዲስ አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ የሚገባ ስሆን፡፡
ውልዋሎ በአነፃሩ 4-5-1 በሆነ የመልሶ ማጥቃት አሰላለፍ በመጠቀም ውጤት ይዞ ለመወጣት ወደ ሜዳ እደሚገባ ይጠበቃል፡፡
ተከላካዩን ተመስገን ካስትሮን ና አማካኙን እንዳለ ከበደን ለብሔራዊ ብድን ያስመረጠው አርባምንጭከተማ አንድነት አዳነ (ማንጋላ) በቅጣት አንበሉን አማኑኤል ጎበና ና አጥቂውን ተሾመ ታደሰ(ክሮች) በጉዳት የሚያጣ ስሆን፡፡
በውልዋሎ በኩል ግብ ጠባቂው በረከት ለብሔራዊ ብድን በመመረጡ እማይኖር ሲሆን ቡሩክ አየለ እና እዮብ ወልደማርያም በጉዳት ምክኒያት ወደ አርባምንጭ ሳይጓዙ መቀረታቸው ሲሰማ፤
ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት ያጋጠመው በረኛው ዘውድ መስፍንም ከነጉዳቱ ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል
በዛሬው እለት ሁለቱም ብድኖች የመጨረሻ ልምምዳቸውን በማድረግ ለነገው ጨዋታ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡