መነሻ ገጽ Uncategorized የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ
Uncategorized

የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

አጋራ
አጋራ

 ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በካፍ የምስረታ በዓልና በጠቅላላ ጉባኤው ላይ በእንግድነት ለመገኘት ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉንና 39ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ያካሂዳል።

ከፕሬዝዳንቱ በተጨማሪ የፊፋ ዋና ጸሐፊ ፋትማ ሳሙራ ለዚሁ ጉባኤ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እና ፋትማ ሳሙራ በጉባኤው ላይ በእግር ኳስ ስፖርት ልማት ላይ ያተኮሩ የሃሣብ ልውውጦች እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተለይም ዋና ጸሐፊዋ የፊፋ ክፍለ አህጉራዊ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ በሚቋቋምበት አግባብ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ጋር ለመምከር ኘሮግራም ይዘዋል፡፡

ፊፋ በአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት ከመክፈት በተጨማሪ ተከታታይ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር እርስቱ ይርዳ፣ ሚኒስትር ዴኤታው ተስፋዬ ይገዙ፣ እንዲሁም የካፍ ኘሬዝዳንት ኢሣ ሃያቱ እና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች ለእንግዶቹ አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...