መነሻ ገጽ Uncategorized ​የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ማርት ኖይ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው በፊት ሶዌታን ላይቭ ከሚባል ድረ ገጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡አሰልጣኙ ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ስለ ነበራቸው ጨዋታ እና ከጨዋታው ጋር ተያያዥነት ስላላቸው ሁነቶች ቆይታ አድርገዋል፡፡
Uncategorized

​የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ማርት ኖይ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው በፊት ሶዌታን ላይቭ ከሚባል ድረ ገጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡አሰልጣኙ ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ስለ ነበራቸው ጨዋታ እና ከጨዋታው ጋር ተያያዥነት ስላላቸው ሁነቶች ቆይታ አድርገዋል፡፡

አጋራ
አጋራ

«የእናንተ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሆኑት ዲኤስቲቪ እና ሱፐር ስፖርት
ሰንዳውንስ ምን እየሰራ እንዳለ ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም
በጨዋታው ላይ እኔ ምንም ያስደነቀኝ ነገር የለም፡፡»
ጋዜጠኛው አሰልጣኝ ማርት ኖይ በ2012 ከኬፕታውን ሳንቶስ ጋር
መቆየታቸው እና የደቡብ አፍሪካን አብሳ ፕሪሚየር ሺፕን ማወቃቸው
ለጨዋታው እንደረዳቸው ሲጠይቃቸው አሰልጣኝ ማርት ኖይ
የመለሱት እንዲህ በማለት ነበር፡፡

«በሚገባ ረድቶናል፤ ነገር ግን ላለፉት 17 አመታት አንስቶ እስከ አሁን
ድረስ በአፍሪካ ውስጥ ነኝ፡፡ በ6 አገራት በአሰልጣኝነት ሰርቻለሁ፡፡
በመሆኑም ተጨዋቾቼ ካላቸው የኢንተርናሽናል ጨዋታ ልምድ የተሻለ
እኔ አለኝ፡፡ በዚህም ምክንያት የተነሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ
እኔን መርጦኛል፡፡ እኔም ደስተኛ ነኝ፡፡»
እኔ ሆላንዳዊ አሰልጣኝ ነኝ፡፡ በእኛ የአሰልጣኝነት ትምህርት ውስጥ
የጨዋታ ትንተና በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በመሆኑም ከራሴ ሰዎች ጋር
በመሆን ከጨዋታው በፊት የሰንዳውንስን ጨዋታ መርምሬያለሁ፡፡ እኛ
ለእያንዳንዱ ጨዋታ የራሳችን ሰው እንልካለን፡፡ በመሆኑም በቱኒዝ
የራሳችን ሰው አለን፡፡
ጋዜጠኛው ይቀጥላል፡፡ ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ በእናንተ የመልበሻ
ክፍል ውስጥ የሚሰማው ደማቅ የደስታ አገላለጽ ያልጠበቃችሁትን
ውጤት ማሳካት እንደቻላችሁ የሚያሳይ ነበር፡፡
«ይህ የአቻ ውጤት ለእኛ ድል ነው፡፡ የተጫወትነው ኳስን በአጭር
ቅብብል እና በፍጥነት ከሚጫወት ቡድን ጋር ነው፡፡ ይህንን እኛ
በአገራችን ውስጥ መጠቀም አለመድንም፡፡ በመሆንም ይህ ለእኔ
ተጨዋቾች ትልቅ ልምድ ይሆናቸዋል፡፡»
«በመሆኑም ሰንዳውንስን ማቆም በመቻላችን እና ይህ
አጨዋወታችንን ሊሰበሩ ባለመቻላቸው ኩራት ይሰማኛል፡፡ በእኔ
አመለካከት ቅርጻችንን ጠብቀብ እና በጣም ተደራጅተን
ተጫውተናል፡፡»
Source-የፈረሰኞቹ ገፅ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...