መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ሀዋሳ ከተማኢትዮ-ኤሌክትሪክዳሰሳ

የጨዋታ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11 ሳምንት መርሀግብር እሁድ ከሚደረጉ 6 ጨዋታወች መካከል ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያስተናግዳል፡፡

ሀዋሳ ከተማ ካደረጋቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ማግኝት ከሚገባው 6 ነጥብ 1 ነጥብ ብቻን ማግኝት ሲችል፡፡
እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተከታታይ ባደረገው ሁለት ጨዋታ ሽንፈትን በማስተናገድ በወራጅ ቀጠናው አርባምንጭ ከተማ በአንድ ደረጃ በመብለጥ ሊቀመጥ ችሏል፡፡

የቀድሞ የብሔራዊ ብድን አሰልጣኝ የነበሩትን አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ከወራጅ ቀጠናው ለመወጣት የሚጫወቱ ሲሆን በኮከብ ግብ አግቢ ተጫዋቾች መሪ ላይ በሚገኝው ካሉሻ አልሀሰን በመታገዝ እንዲሁ ቡድኑ በጥቂቱ በሚያሳየው በአንድ ሁለት ቅብብል በመጫወት ውጤት ይዞ ለመወጣት እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ሀዋሳ ከተማ ተመልካችን በሚያዝናና አና በሚያምር የኳስ አጨዋወት የሚጫወት ቡድን ሲሆን ልምድ ባለቸው ና በታዳጊ ተጫዋቾች የተዋቀረ ቡድን በመሆኑ በሜዳው እንደመሆኑ መጠን በተጋጣሚው ላይ ድልን በማስመዝገብ ከመሪወቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡

ባለሜዳወቹ ሀዋሳወች ከደረጉት 10 ጨዋታ 12 ነጥብ በመሰብሰብ 7ደረጃን በመያዝ በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ ሲቀመጡ፡፡
ተጋጣሚያቸው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ካደረጋቸው 9 ጨዋታወች 8 ነጥብ በመያዝ በሊጉ ሰንጠረዥ ከአርባምንጭ ከተማ አንድ ደረጃ ከፍ በማለት 15 ደረጃ ሊይዙ ችለዋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ በኩል
ያቡን ዊሊያም፣ ጋናዊው ተከላካይ ላውረንስ ላርቴ፣ ዳንኤል ደርቤ እና አዲስአለም ተስፋዬ በጉዳት ከጨዋታ ወጪ ስሆኑ ዳዊት ፍቃዱ በጨዋታው ሊገባም ላይገባም ሲችላል፡፡
ፍቅረኢየሱስ ተ/ብርሀን በቅጣት ማያሰልፍ ይሆናል፡፡

በኢትዮ-ኤሌክትሪክ በኩል
አወት ገ/ሚካኤል፣ ሱሌማን አቡ፣ ቢንያም አሰፋ፣ ኃይሌ እሸቱ እና ዘካሪያስ ቱጂ በጉዳት እንዲሁም
በኀይሉ ተሻገር(አኪራ) በቅጣት የነገው ጨዋታ የሚያልፋቸው ይሆናል፡፡

የነገውን ጨዋታ ፌ/ዳኛ ሀብታሙ መንግስቴ የሚመራው ይሆናል፡፡

የዛሬ አመት ሁለቱ ብድኖች ተገናኝተው 1-1 በሆነ የአቻ ውጤት ተለያይተው፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀዋሳ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ኢትዮጵያ ቡና ቢሮ ገብቶ በድንገት ለሀዋሳ የፈረመው ግብ ጠባቂ። በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ...

ሀዋሳ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

  ከሸገር ከተማ ጋር የተለያየው አድናን ረሻድ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቀለ። በጅማ አባጅፋር...