መነሻ ገጽ አርባምንጭ ከተማ የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ | አርባምንጭ ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር
አርባምንጭ ከተማዳሰሳጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ | አርባምንጭ ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር

አጋራ
አጋራ

8ኛ ሳምንት ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዳሜ እሁድ ና ሰኞ በሚደረጉ የጨዋታ መርሀግብሮች ቀጥለው ሲውሉ፡፡ ወደ ሰኞ የቀን ለውጥ የተደረገው አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከተማ ከአዲስ አዳጊው ጅማ አባጅፋር ሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡በዚህም ጨዋታ ላይ የተወሰኑ ነጥቦችን እናያለን፡፡
የመጀመሪያ 4ጨዋታወችን በውጤት ቀውስ ውስጥ የነበሩት አዞዎቹ በ5 ሳምንት መርሀግብር መከላከያን በማሸነፍ በጥቂቱ እፎይታን ማግኝት ቢችሉም በ6ኛ ሳምንት ከውልዋሎ.ዓ.ዩ ጋር  1-1 በሆነ የአቻ ውጤት እንዲሁም በ7 ሳምንት በቅዱስ-ጊዮርጊስ የ3-0 ሽንፈትን በማስተናገድ ተመልሶ ወደ ውጤት ቀውስ ውስጥ ሊገባ ችሏል፡፡

በአንፃሩ ጅማ አባጅፋር በመክፈቻው ጨዋታ ሐዋሳ ከተማን በማሸነፍ በድል ቢጀምርም ባደረጋቸው 5 ተከታታይ ጨዋታዎች በውጤት ና በጎል ድርቅ ሲመታ ቆይቶ በ7 ሳምንት መርሀግብር ጅማ ላይ ኢትዮጵያ ቡናን በኦኪኪ አፎላኒ ና ተመስገን ገ/ኪዳን 2ግቦች 2-0 በማሸነፍ 2ኛ ድሉን ማሳካት ችሏል፡፡

የአሰልጣኝ ገ/መድን ሀይሌው ስብስብ አባጅፋር በሔኖክ አዱኛ ና በዮናስ ገረመው አማካኝነት ኳስን መሰረት ያደረገ አንዲሁም በመስመር ፈጣን መልሶ ማጥቃት የሚጫወቱ ተጫዋቾችን የያዘ ቡድን ሲሆን በተደጋጋሚ ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል የሚደርሱት አጥቂዎቹ ተመስገን ገ/ኪዳን ና ኦኪኪ አፎላኒ ከአርባምንጭ ከተማ የመስመር ተጫዋቾች ና ተከላካዮች ጋር የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ የፀጋዬ ኪ/ማርያሙ አርባምንጭ ከተማ በወንድሜነህ ዘሪሁን ና ተካልኝን ደጄኔ አማካኝነት በሚመሰረቱ አጭር እና እረጅም ኳሶች አንዲሁም  በአጥቂው ብርሀኑ አዳሙ የግል ብቃት ወደ ጎል የሚደርስ ቡድን በመሆኑ የሰኞውን ጨዋታ ተጠባባቂ ያደርገዋል፡፡

በሁለቱም በኩል ከብሔራዊ ብድን የተመለሱ ተጫዋቾችን በ7 ሳምንት የጨዋታ መርሀግብር የተጠቀሙ ሲሆን በዚህም ጨዋታ ላይ ለየቡድናቸው ግልጋሎታቸውን እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

የአንበሉ አማኑኤል ጎበና ና የተሾመ ታደሰን ግልጋሎት  በጉዳት ምክንያት የማያገኝው አርባምንጭ ከ4 ጨዋታወች ቅጣት በሃላ አንድነት አዳነን ግልጋሎት የሚያገኝ ይሆናል፡፡

በጅማ አባጅፋር በኩል በጉዳት ሆነ በቅጣት እሚያጣቸው ተጫዋቾች የሉም፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባጅፋር በ5 ጨዋታወች 8ነጥብ በመሰብሰብ 8ደረጃ ላይ ሲገኝ፡፡ አዞዎቹ ከ7 ጨዋታወች 6ነጥብ በመሰብሰብ 13ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
አርባምንጭ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

ከደቂቃዎች በፊት ጋናዊው አጥቂ ያስፈረሙት አዞዎቹ ሴኔጋላዊውን ተጫዋች አራተኛ ፈራሚ አድርገዋል። የቀድሞው...

አርባምንጭ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

አዞዎቹ በአጋማሹ የዝውውር መስኮት ሦስተኛ ፈራሚያቸው ታውቋል። በአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ የሚመራው አርባምንጭ...