ማስታወቂያ አውጥቶ የነበረው አርባምንጭ ከተማ አዲስ ስራ አስኪያጅ በሀላፊነት ሾሟል።

ከወራቶች በፊት በክለቡ አሰራር ብልሽት ምክንያት የለቀቁት አቶ ዳዊት ሀይለማርያምን ለመተካት የስራ አስኪያጅ ሹመት ማስታወቂያን አውጥቶ የነበረው አርባምንጭ ከተማ አቶ ወንድይፍራው ወርቅነህ ክለባችን በቦታው መቅጠሩን አሳውቋል።
ሁለተኛ ድግሪ በስፖርት ሳይንስ ህክምና ያላቸው እና በኮንሶ ልዩ ወረዳ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ በሀዋሳ ቢ ኤን ቢ በመምህርነት ፣ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በስራ ሂደት አስተባባሪነት በቦንጋ እና በጂንካ ዩኒቨርስቲ በስፖርት ሳይንስ ት/ት ክፍል መምህር በመሆን አገልግለዋል ያገለገሉ ሲሆን በስፖርት ዘርፍ ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ የአሰልጣኝነት እና በፌደራል ዳኝነት ሰርተፍኬት ያላቸው ሲሆን በቀደመው የደቡብ ክልል የእግር ኳስ ፌደሬሽን ውድድር በአሰልጣኝነት የሰሩ ሲሆን በመጨረሻም አዲሱ የአርባምንጭ ስራ አስኪያጅ ሆነው በቦታው ተሹመዋል።
አስተያየት ይስጡ